Get Mystery Box with random crypto!

Top students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_schools — Top students T
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_schools — Top students
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_schools
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 548
የሰርጥ መግለጫ

#ፈጣን እና ታማኝ የመረጃ ምንጭ
#FOR FRESHMAN @freshman_exam
#FOR 9-REMEDIAL @high_preparatory
#ዉብቷ ሀገር :- ኢትዮጵያ
#አዲስ_አበባ
ለአስተያየት / ለማስታወቂያ
@mulea27

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2023-02-07 14:06:20 ►ብዙን ጊዜ Final Exam የሚወጣበት መጽሐፍ ነዉ ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው !

Meriam Engineering Mechanics.

Frequently used by University Lectureres.

For Engineering Students
በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
5.3K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 14:06:04 ASTU ( Adama Science and Technology University )

የScience እና Technology  ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ እሚሰጣቸው Departmentoch ውስን ናቸው ማለትም Engineering እና Applied Science ፊልዶች ብቻ ናቸው ።

በ Engineering ስር 3 Schooloችን 
1-School of Electrical
2-School of Mechanical
3-School of Civil and Architecture

በእነዚህ schoolችም ስርም ፦


1.School of Electrical computing ስር
-Software engineering
-Computer science and engineering(CSE)
-Power and Control
-Communication and Electronics


2.በSchool of Mechanical chemical and material ስር
- Mechanical engineering
-Chemical engineering
-Material Science and Engineering


3.በSchool of Civil and Architecture ስር
-Civil engineering
-Architectural engineering
-Water engineering
-Geomathics engineering
    


በApplied Science ውስጥ ፦

-Applied Maths
-Applied Chemistry
-Applied Physics
-Geology
-Industrial chemistry
- Pharmacy


ወደ ዩኒቨርስቲው ለመቀላቀል ፈተና ያለው ሲሆን እሚቀበላቸው ተማሪወች ውስን ናቸው ተማሪ እምንቀበለው በ Laboratoryኣችን ልክ ነው ብለው ስለሚያምኑ ! በጠቅላላ ግቢው ውስጥ ከ Fresh እስከ Masters 7000 ተማሪወች 2000 ሰራተኞች ይገኛሉ ።


ተማሪወች ትንሽ ከመሆናቸው አንፃር ምግብ ከየትኛውም ግቢ የተሻለ ነው ። 

library

1-Central Library
2-Applied Library
3-Liberal arts library
4-Post graduate library
5-Females library

እንዲሁም በየdepartmentቶች  የየራሳቸው library ያላቸው ሲሆን የሴቶቹ ለብቻቸው እሚጠቀሙበትም አላቸው ።ሌላው ነገር libraryወቹ በውስጣቸው በጣም ፈጣን WiFi እና Computer አላቸው ። ግቢው ለሚጠቀምበት በጣም ብዙ laboratoryወች አሉ ።

DSTV በኮሮና ተዘግቶ ቆይቶ በቅርቡ የጀመረ ነው ግቢው ውስጥ Anfi እሚባል ቦታ አለ እዛ ላይ በ cinema standard led screen አለ እንዲሁም ሶስት ቦታወች ላይ አነስተኛ screenoch አሉ ። ለሴቶች ትንሽ ሻል ያለ አገልግሎት ይሰጣል በዶርመተሪ በlibraryም በብዙ ነገር ይጠቀማሉ !


የራሱ ውሀ ማጣሪያ ያለው ሲሆን ፤ ብዙም የውሀ ችግር የለም መብራት አይጠፋም ከጠፋም በ 5 ደቂቃ ውስጥ እሚነሳ automatic generator አለ ። Dormitory አሪፍ  የሚባል ነው ።  የግቢ መግቢያ ሰዓት 3:00 ከሌሎች የተሻለ ነው ። ሌላው በፍፁም ሰው እማይተናኮሉ ለማዳ ለመባል እሚቀርቡ ጅቦች አሉ ፤

በጣም ጠቃሚ ነገር

ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ነው ት/ት እሚሰጠው ለምሳሌ Comon course እሚባል ነገር የለም engineering እሚገባ ቀጥታ pre engineering ይማራል  Appliedም እንደዛው ነው ።

Gpa ከ 3.5 በላይ ካለ እና ሌላ ፊልድ ደርቦ መመረቅ ለሚፈልግም dual degree ይሰጣል ሁለት degree ማለት ነው ።  International degree መስጠትም እጀምራለሁ ብሎ ለ2013 ባች ቃል ገብተዋል። 


ማስጠንቀቂያ

ግቢው በ ት/ት ጉዳይ አይደራደርም ፈተናቸው አስመራሪ ነው ግን በደምብ ለመስራት ለሚመጣ ተማሪ እሚከብደው አይሆንም !

CREDIT:ዘ campus


For all 2015 freshman students join our telegram channel
On our channel you get:
2015 EUEE university info.
fresh man first semester handouts
first semester mid and final exams
first semester short notes
COC exams for medicine, other health,


በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
3.7K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 14:05:42 #Repost

በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎች የ መጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።


የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች

Communicative English Skill I

Anthropology

Economics

Geography

Maths(Social)

Civics and Moral Education

Global Trends

Physical Fitness

አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።

Communicative English Skill I

ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። ነገር ግን የአምና ተማሪዎች ውጤታቸውን ዝቅ አድርጎባቸዋል። በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት

Reading skill ( ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።)

Grammar( Active and pasive voice , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ።) mid exam, final exam እና CoC exam ላይ passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)

Vocabulary - ከ አውዱ ተነስታችሁ የቃላቶችን ተመሳሳይ ና ተቃራኒ ትርጉም መፈለግ ነው። ብዙ ተማሪዎች ለመስራት ይቸገራሉ ፤ ፈተና ላይ በብዛት ይወጣል። ኮርሱ A+ tutorial class ላይ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Economics

የ Economics ትምህርት ፈተናዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ለዚህ ኮርስ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ቲቶርያል ልጠቁማችሁ። በርግጠኝነት A+ ነው የምታመጡት። Fortino Academy ይባላል። በ አማርኛ እያብራራ ያስረዳል። እጅግ በጣም ሲበዛ ግልፅ ና ለፈተና የሚያዘጋጁ ትምህርቶች ይቀርቡበታል። You tube ላይ ገብታችሁ ተከታተሉት።

Geography

በዚህ ኮርስ የኢትዮጵያን ና የምስራቅ አፍሪካን ገፅታ ትማራላችሁ። ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ :: አደራ ይህን ኮርስ እንዳትንቁት ከባድ የሚባል ና ብዙ ፍሬሾችን የሚያስቸግር ኮርስ ነው።

Maths (Social)

ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

Civics and Moral Education

ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በተጨማሪም ስለ Constitution, Democracy ና Human Right በጣም በስፋት ያጠናል ። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Global Trends

ይህ ኮርስ ከስሙ እንደምትረዱት ፤ ፖለቲካዊ ቴክኖሎጂያዊ ና ኢኮኖሚያው አለም አቀፍ ጉዳዮችን ይዳስሳል። በተለይ አለም አቀፍ ግንኙነት(International relation) ሳይንሳዊ ምንነትን ይዳስሳል። ስለ አቀፍ ግንኙነት ንድፈ ሀሳቦችን ይዳስሳል በተለይ ስለ Liberalism, Realism , Marxism ና Constructivism የተባሉ የፖለቲካ ርዕዮቶችን ይዳስሳል። እንዲሁም ስለ Foreign Policy, National interest ና Globalization በሰፊው ይናገራል። ይህ ኮርስ ለተማሪዎች የሚከብድ ኮርስ ነው። A+ Tutorial Class ላይ በጣም ደስ በሚል ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Anthropology

ለ theory ተማሪ ይህ ኮርስ ደስ የሚል ነው። በዋናነት የሚያጠና ስለ ሰው ልጅ አመጣጥ ፤ ስለ culture ፥ Ethinicity ፥ Social Norms ነው። A+ Tutorial Class ላይ በአሪፉ ስለሚሰጥ ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Physical Fitness

ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል።

በአብዛሀኛው ግቢ የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው።

በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
3.5K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 14:05:25 #Repost

በቀጣይ ግቢ የምትገቡ የ ተፈጥሮ ሳይንስ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።

በ Daniel Th and Daniel Sh ተፅፎ በ Concise English(@Aconcise) ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ።

የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች


MATHEMATICS ( for natural science)

GENERAL PHYSICS

GEOGRAPHY

LOGIC & CRITICAL THINKING

COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL I

PSYCHOLOGY

PHYSICAL FITNESS

እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት።

MATHS

11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው።

በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::

Logic and critical thinking

ይህ course ለእናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው ። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም ።

ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።

1ኛ) Concise introduction to logic

2ኛ) freshman logic

Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት ። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን ፈተና ትሰሩታላችሁ ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል ። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው ።

Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ ። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት ። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ

1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት። A+ tutorial Class ላይ ትምህርቱ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ እዛ ላይ ተመዝግባችሁ መማር።

2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።

3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት ። ከዛ A ታመጡና መቀወጥ ።

Communicative English skill I

ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡ ። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ

Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%)

Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።)

ኮርሱ A+ tutorial class ላይ እጅግ በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ይሰጣል ብዙ ተማሪዎችም A+ አምጥተውበታል ተመዝግባችሁ ተማሩ።

Geography

ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ ::

Psychology

ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል:: ይህ ትምህርት ለየትው የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል Module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም Module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Google ማድረግ በጣም ተመራጭ ነው በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ Case ጥያቄ ስለሚበዛ በደም Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል በቀላሉ Google ላይ በ Topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ ከፈተናው ተመሳሳይ ጥያቄ ታገኛላቹ።
ሌላኛው አማራጭ YouTube ነው እኛ ሀገር በስፋት ባይለመድም በአጭር ግዜ Concept ለመረዳት ፍቱን ነው ሞክሩት ።
11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩ ነው አታስቡ A+ የናንተ ናት ኮርሱ A+ tutorial class ላይ እጅግ በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ይሰጣል ብዙ ተማሪዎችም A+ አምጥተውበታል ተመዝግባችሁ ተማሩ።

General Physics

General physics የምትማሩት ከ 11 እና 12 የተለየ ነገር የለውም ከናንተ የሚጠበቀው Module ማንበብና የተወሰነ Refer አድርጋቹህ ጥያቆዎችን መስራት ነው እንጂ የተለየ አዲስ ነገር የለውም::

Physical fitness

ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው ። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ ። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም:: pass or fail ነው የምትባሉት።

በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
4.5K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 21:17:05
Jimma_university
Anthropology Final exam(2013)

በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
7.8K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 21:17:05
Dilla university.
civic final exam last year

በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
6.0K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 21:17:05
Jimma University.

Civics Final Exam Last year.

በየትምህርት ቤታችሁ group ላይ ሼርርርርርርርርርር አድርጉት

TOP STUDENTS " TOPPERS HOME"

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
5.9K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 12:15:13 በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ተፈጥሮ ሳይንስ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ ።

የመጀመሪያ አመት የመጀመራያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች


  MATHEMATICS ( for natural science)

GENERAL PHYSICS

GEOGRAPHY

LOGIC & CRITICAL THINKING

COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL

PSYCHOLOGY

PHYSICAL FITNESS

እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች
እንመልከት።

    MATHS

11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው። ስለዚህ ብዙም አትቸገሩበትም ፡ አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ ። A+

        General Physics

ይኸም 11 ኛ እና 12 ኛ የተማራችሗቸው ናቸው አብዛኞቹ ።

Logic and critical thinking

ይህ course ለእናንተ አዲስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ እና English ቋንቋ የምትሞክሩ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው ። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም ።

ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።

1ኛ) Concise introduction to logic

2ኛ)  freshman logic

Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት ። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን  ፈተና ትሰሩታላችሁ ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል ። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው ።

Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ ። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት ። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ

1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት።

2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።

3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት ። ከዛ A+ ታመጡና መቀወጥ ።

Communicative English skill

ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡ ግቢ ላይ ውጤታችሁን ከሚያነሱ ኮርሶች መካከል ነው ። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ

Speaking skill ( ራሳችሁን በ እንግሊዝኛ ማስተዋወቅ ፡ ከዛ መምህሩ የሆነ ርዕስ ይሰጣችሁ እና ስለዛ ነገር በ እንግሊዝኛ presentation ማቅረብ (የሆነ ማርክ%)

Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%)

Writing skill ( letter , descriptive , narrative,argumentative , expository ከነዚህ ባንዱ ትፅፋላችሁ( ከዛ የሆነ ማርክ)

Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።)

     Geography

ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም።

   Psychology

ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል ፡ ግን biology ማንበብ ስለለመዳችሁ አትቸገሩም። theory ነው ፡ ከእናንተ የሚጠበቀዉ ማንበብ ብቻ ኘው።

   Physical fitness
,
ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው ። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ ። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም ዝም ብላችሁ ሜዳ ወታችሁ ትሰራላችሁ እንጅ Grade ( A , A- , B+ ,B , C ....) የለውም። pass or fail ነው የምትባሉት። Attendance ወይም በዚህ ኮርስ ክፍለ ጊዜ ካልቀራችሁ pass ትሆናላችሁ።

እሽ እስከአሁን የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸውን ኮርሶች አየን።

ነገር ግን  አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ በ Logic and critical thinking ቦታ emerging technology የሚያስተምሩ አሉ ። ከዛ second semester ላይ ደግሞ logic and critical thinking ያስተምራሉ። ብቻ ምንም ለውጥ የለውም ፡ እንድታውቁት ያክል ነው።

  Emerging technology

ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ አይደለም። ከ 9 - 12 የተማራችሗቸው የ Ict ትምህርቶችን ያካትታል ( Ms word , Ms PowerPoint, Ms excel , database ..... ወዘተ)


በቃ አለቀ። እነዚህን ኮርሶች ወስዳችሁ እንደጨረሳችሁ

ህክምና ( Medicine , Dental Medicine , Veterinary medicine , pharmacy...) መግባት የምትፈልጉ

ቴክኖሎጂ( Engineering, Architecture, Computer science, It , software engineering...) መግባት የምትፈልጉ

Coc exam ተፈትናችሁ ትገባላችሁ ማለት ነው።

ለማስታወስ ያክል

First semester ( 50%)
Coc exam ( 30%)
Entrance exam( 20%)

computational science ( Physics , Chem , bio , maths , biotechnology...)

Other health ( medical laboratory, nursing , midwifery....)

መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ የመጀመሪያውን አመት( የመጀመሪያ ሴሚስተር አይደለም) እንደጨረሳችሁ ትገባላችሁ።

በመጨረሻም የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸውን ኮርሶች እና አጋዥ መፅሀፍ በ PDF ከባለፈው የቀሬ ቀጣይ እንልክላችሗለን።

በቀጣይ ደግሞ የ social science Course እናያለን!


@ethio_schools
7.8K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 16:55:07
2.5K viewsDaniel Thomas, 13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:28:31 Royal Civics & Ethical Education
for Grade 11 & 12

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share


@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools
3.8K viewsMulea JR, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ