Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ። በ | SCHOOL ላይብረሪ

#Update

የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ።

በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል። 

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት ፈተና መወሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ተፈራ አብራርተዋል።

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ሁለተኛ ዙርም በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ፈተናው በሰላም መጠናቀቅ እንዲችል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።