Get Mystery Box with random crypto!

አንቸሎቲ PREE - MATCH PRESS CONFRERES ! 'ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ጨዋታው | ኢትዮ ሪያል ማድሪድ

አንቸሎቲ PREE - MATCH PRESS CONFRERES !

"ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ጨዋታውን በትኩረት መጀመር አለብን እናም በምንም አይነት ሁኔታ በመጀመሪያው ጨዋታ 5-2 እንዳሸነፍን አስበን ወደ ሜዳ አንገባም። በእርግጠኝነት በመከላከል ላይ ያተኮረ ጨዋታ አንጫወትም እናም ሜዳ ላይ ዝግ የሆነ ጨዋታ አታዩም። ተጨዋቾቹ ከፊት ለፊታችን ምን አይነት አስፈላጊ ጨዋታ እንዳለን ይገነዘባሉ።"

"ሊቨርፑል ነገም ዳግመኛ የሚሸነፍበት ነገር የለም ለዚህም ነው በጣም አስቸጋሪ ጨዋታ ይኖረናል ያልኩት። በአንፊልድ የተከሰተዉን ለማካካስ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ወደ ሜዳ ይገባሉ እኛም በዚህ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ሊቨርፑልን በፍፁም ገምተን ወደ ሜዳ አንገባም።"

"ነገ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾች እና ወጣት እና ጉልበት ያላቸው ተጨዋቾች በጣምራነት እንፈልጋለን። ካማቪንጋ በጣም ጥሩ የሆነ ብቃቱን ለተመልካች ያቀርባል። አዎ በኤስፓኞል ላይ ስህተት ሰርቷል ነገር ግን በጥሩ ሁኔታ በመጫወቱ ስህተቶቹ ጎልተዉ እንዳይታዩ አድርጓል። አሁን በቡድናችን ዉስጥ ያለ ተፅእኖ ፈጣሪ ተጨዋች ከሆኑት ዉስጥ አንዱ ነው እናም ይቀጥላል።"

ከሀዛርድ ጋር ስለተደረገዉ ቃለ ምልልስ ፦

"ሀዛርድ ሁሉንም ነገር በቅንነት ተናግሯል። አዎ ብዙ አናወራም ይህ ምናልባት በልዩ ማንነቱ የተነሳ ሊሆን ይችላል። ከሁሉም በላይ በመካከላችን መከባበር አለ። ኤዲን አሁን ላይ አይጫወትም ምክንያቱም ቪኒሲየስ በእሱ ቦታ ጥሩ ስራ ሰርቷል እና በአለም ላይ ካሉት ምርጥ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው። ካሪምም መቶ በመቶ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል።"

@ETHIO_REAL_MADRID_14
@ETHIO_REAL_MADRID_14

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+Uogf2-3bOBjpolkk