Get Mystery Box with random crypto!

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተደረገ | ETHIO NEWS

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተደረገ

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ  መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሪ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በታሪፍ ቁጥር 9401. 9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣

2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና

4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች

የውጭ ምንዛሬ ክልከላው እንደማይመለከታቸው ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር  2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው።