Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ | ETHIO NEWS

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይም እንደመከሩ አስታውቀዋል።

በውይይቱ አገራቱ በመከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ ማድረግ ትልቅ ጥቅም እንዳለው መስማማታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

@Skyline7777
@Skyline7777