Get Mystery Box with random crypto!

#ቂሷ *ክፍል_1* #የዳናወቹ_ቂሷ | 🖋የኛ📖ብዕር🖋

#ቂሷ
*ክፍል_1*

#የዳናወቹ_ቂሷ
በእለታት አንድ ቀን እጁ የተቆረጠበት ሰውየ ወደ ዳናወቹ ሸይኽ መጣ ከዚያም ለነዛ ሸይኽ እንዲህ አላቸው ያሸይኽ እባካችሁ ይሄን እጄን መላ በሉልኝ አላቸው

እነሱም የተቸገርን መርዳት እንዳለባቸው ስለሚያውቁ ናተሎ ጠጋ በለኝ አሉት ሰውየውም ተጠጋቸው ከዚያም ያን የተቆረጠ እጅ ሰከንድ ባልሞላ ሰዐት ቀጠሉለት

ሰውየውም በመገረም ምን ብላችሁ ነው በዚህ ፍጥነት እንደዚ ድሮ እንደነበረ ያደረጋችሁት አላቸው እነሱም ጃሂል እንደነበረ ስለሚያውቁ ተው ይቅርብህ ዝም ብለህ ሂድ አሉት

እሱም እንደው ካልነገራችሁኝ አልሄድም አለ ዝም ብሎ እንዲሄድ ደጋግመው ቢነግሩትም ሊሰማቸው አልቻለም

እነሱም ከእንግዲህ እንቢ ካልክ ልንገርህ አሉና
ያልኩት
#ቢስሚላሂ_ሮህማኒሮሂም ነው አሉት
እሱም በመገረም 
#ብቻ ሲል  ያ የተቀጠለለት እጅ ወዲያዉኑ እርግፍ አለ።

ይህ ቂሷ የምር የተከሰተ ነው አሏህ በጊዜ በቦታ እንዲሁም በሰው ላይ በረካውን ለየት ለየት አድርግ አስቀምጧል ለምሳሌ ከቦታ ሁሉ በላጩ መስጂድ ነው። ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የአረፋ ቀን ነው። ከለይሎች ሁሉ በላጩ ለይለተል ቀድር የምትታይበት ለይል ነው። እንዲሁም አሏህ ለሚወዳቸው ሰዎች እሱን ለሚገዙት ብቻ ለየት ለየት አድርጎ የሚሰጣቸው ከራማ አለ እሳቸውም ከነዛ ውስጥ ስለነበሩ ነው ።

    ከዚ ቂሷ ምን እንረዳለን

1  ጥያቄ ማብዛት እንደሌለብን
2  በተደረገልን ነገር ማመስገን እንዳለብን
3  የአሏህ ስሞች ምን ያክል ጠቃሚ እንደሆኑ የአሏህን ስም አቅለን ማየት እንደሌለብን ሌሎች ሌሎችም አሉ ።

    አሏህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን

https://t.me/Eslmnachin99

https://t.me/sufiyahlesuna