Get Mystery Box with random crypto!

ከእለታት በአንዱ ቀን ላይ ኢብራሂም ኢብን አድሀም ለሀጅ ጉዞ በእግራቸው ወጡ፣ በመንገዳቸው ላይ አ | Ethio🇪🇹Muslim🇪🇹 Nashida - Menzuma 🎼

ከእለታት በአንዱ ቀን ላይ ኢብራሂም ኢብን አድሀም ለሀጅ ጉዞ በእግራቸው ወጡ፣
በመንገዳቸው ላይ አንድ ሰው ከፈረሱ ላይ ሆኖ አያቸውና
"ኢብራሂም ሆይ ወዴት እየሄዱ ነው?" አላቸው??
"ወደ ሀጅ" ሲሉ መለሱለት
"መጓጓዣዎት የት አለ መንገዱኮ ረዥም ነው??" አላቸው
"ስለማይታይህ ነው እንጅ ለእኔ ብዙ መጓጓዣ አለኝ" አሉት
"የት አሉ?" ሲል ጠየቀ
♡ሙሲባ በእኔ ላይ ከወረደ የትእግስት መጓጓዣየ ላይ እወጣለሁ!
♡ኒዕማ በእኔ ላይ ከወረደ የምስጋና መጓጓዣየ ላይ እወጣለሁ!
♡የአላህ ውሳኔ በእኔ ላይ ከመጣ ፍርዱን የምወድበት መጓጓዣየ ላይ እወጣለሁ!!
ሰውየውም "በአላህ በረካ ጉዞህን ቀጥል! አንተ ተጓዥ ነህ እኔ ተራማጅ ነኝ" አላቸው።

@Ethio_muslim_nashida

ማንኛውም ጥያቄ ሲኖራችሁ በፍጥነት ያስፍሩልን
@abudi_junior