Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተጠናቀቀ ............................... | Ministry of Education Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም ተጠናቀቀ

............................................
መጋቢት 8/2016 ዓ.ም (ትሚ) መሪ ቃሉን “ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ” (Higher Education for Higher Impacts) ያረገው የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም ትናንት ተጠናቀቀ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በፎረሙ ማጠቃለያ ከፍተኛ ትምህርት ላይ እየተተገበሩ ያሉት ቁልፍ የለውጥ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ሃላፊዎች በትኩረት በመሰራት የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸውና የሁሉንም ባለድርሻዎች የላቀ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ ከመላው የሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚደንቶችና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች አንዲሁም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ፎረም በተጀመሩ የለውጥ መርሃ-ግብሮች አተገባበር፣የለውጥ ስኬቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ጥልቅ ውይይት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የቀጣይ ስራ አቅጣጫዎች ላይ በመምከር ተጠናቋል፡፡

በዕለቱ በጅማ ዩኒቨርስቲ (@ Jimma University ) የተዘጋጀ አውደርዕይ፣ የዲጂታል ትምህርት ስቱዲዮና Ict መረጃ ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ካምፓሶች በፎረሙ ተሳታፊዎች ተኀብኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ!