Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም እየተካሄደ ነው:: ------------------------- | Ministry of Education Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም እየተካሄደ ነው::
-------------------------//--------------

መጋቢት 7/2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም “ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ/Higher Education for Higher Impacts” በሚል መሪ ቃል በጅማ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ የሚተገበሩ አዳዲስ ሪፎርሞች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በማካሄድ ላይ ነው::

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሸኔ በውይይት መድረኩ ተገኝተው ካለፈው ተሞክሮ ስለተገኙ ቁም ነገሮችና ዘርፉ ያለበትን ቁመና አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል::

ሚኒስትር ዴኤታው ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ለሃገር ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳይኖረው አንቀው ከያዙት ማነቆዎች ሊላቀቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለፎረሙ ተሳታፊዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቂ ነጻነት ፍኖተካርታ፣የዩኒቨርስቲ ትኩረት መስክና ተልዕኮ ልየታ፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር
ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ 1298/2015 ጨምሮ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ላይ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ስላሉ አዳዲስ ትግበራዎችና የለውጥ አጀንዳዎች ዙሪያ የውይይት አጀንዳዎች ቀርበዋል::

በፎረሙ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶችና
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣የትምህርት ሚኒስቴርና የጅማ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ሙሉ ዜናው

https://www.facebook.com/share/p/9C4VF3Qk5MwsoM85/?mibextid=Nif5oz