Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጋበዝ የትምህርት ሚኒስቴር: - 1. | Ministry of Education Ethiopia

ማስታወቂያ

ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጋበዝ

የትምህርት ሚኒስቴር: -
1. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣
2. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣
3. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።
መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ክፍል 2 ንዑስ ክፍል 2 አንቀጽ 10 መሰረት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ አዘጋጀቷል።
በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል።