Get Mystery Box with random crypto!

ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28-30 /2016 ዓ.ም ድረስ በሀገር አ | Ministry of Education Ethiopia

ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28-30 /2016 ዓ.ም ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሠጣል።
...................................//……………………………….
መስከረም 22/2016 ዓ.ም (የትምህርት ሚኒስቴር)
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጠው ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28-30/2016 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ተወካይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ለመማር የብሄራዊ ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሠድ በቅድመ ሁኔታነት መቀመጡን አብራርተዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ሃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚሠጠው ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 ጀምሮ እስከ 25/01/2016 ዓ.ም የሚቆይ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ከመስከረም 23-25/2016 ዓ.ም የልምምድ ፈተና (Mock Exam) የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ተፈታኞች በተመዘገቡበት ዩኒቨርሲቲ በመገኘት User name እና Password በመጠቀም የልምምድ ፈተና መውሰድ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው በተሣካ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ዝርዝር መረጃ የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ፣ https://shorturl.at/jKLR9