Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ሴክተሩ የሚተገበሩ ተግባራትን በህግና ስርዓት መፈፀም እንደሚገባ ተጠቆመ ። ....... | Ministry of Education Ethiopia

በትምህርት ሴክተሩ የሚተገበሩ ተግባራትን በህግና ስርዓት መፈፀም እንደሚገባ ተጠቆመ ።
................................................

መስከረም 13/2015 ዓ/ም (የትምህርት ሚኒስቴር) ለትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በፌድራል አስተዳደር አዋጅ 1183/2012 ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

የስልጠና መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ የሚሠሩ ማናቸውም ስራዎች በህግና በሥርዓት ማስፈፀም ይገባል ብለዋል።

አክለውም በትምህርት ሴክተሩ እየተካሄዱ ያሉት ሪፎርሞች በህግ ማዕቀፍ መተግበር መቻል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በዚህም እንደ ትምህርት ሴክተር በ2015 ዓ.ም በርካታ አዋጆችና ደንቦች መውጣታቸውን አንስተው በቀጣይ በአግባቡ መተግበር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ስልጠናውን የሠጡት ከፍትህ ሚኒስቴር ወ/ሮ ትብለፅ ቡሽራ ይህ ስልጠና በአስፈፃሚ አካላት መካከል ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደሀገር በፍትህ ዘርፉ ሪፎርም ከተካሄደበቸው ህጎች አንዱ መሆኑን አነስተው አመራሩ በትክክል አዋጁን ተረድቶ ማስተግበር ይኖርበታልም ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ይበልጣል አያሌው(ዶ/ር) በበኩላቸው አዋጆችን ተከትለው የወጡ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ሰርኩላሮች የሰዎችን መብት የሚጫኑ ከሆነ በአዋጁ መሠረት ፈጥኖ መፈተሽ እና ማስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናውን የትምህርት ሚኒስቴር ከፍትህ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።