Get Mystery Box with random crypto!

ምስራቅ ሸዋ: የባቡር ሃዲድ ብረቶችን የሰረቀው ግለሰብ ተቀጣ! በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ምስራቅ ሸዋ: የባቡር ሃዲድ ብረቶችን የሰረቀው ግለሰብ ተቀጣ!

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የባቡር ሃዲድ ብረቶች የሰረቀው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጥቷል።

መሐመድ አባተ የተባለው ይሄው ግለሰብ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከለሊቱ 9 ሰዓት የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 - 80256 አ.አ በሆነ አይሱዙ እና ኮድ 3 - 61468 አ.አ በሆነ ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪዎች የዘረፈውን የባቡር ሃዲድ ብረቶች ጭኖ ለመሰወር ሲሞክር በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተነግሯል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግለሰቡ ድርጊት በሰውና ሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ3 ዓመት እስራትና በ4 ሺህ ብር ቅጣት ወስኖበታል።

ግብረ አበሮቹ ለጊዜው ቢያመልጡም ለመያዝ ክትትል እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news