Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ በአዲስ አበባ ከተማ ትናንት ሰኔ 3/2015 ከሰዓት በኋላ 10:06  በንፋስ ስል | ኢትዮ መረጃ - NEWS

አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ ትናንት ሰኔ 3/2015 ከሰዓት በኋላ 10:06  በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኝ  ኢትዮ አታልስ በሚባል መስታወት ፋብሪካ ላይ በደረሰ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል ።

አደጋዉ የደረሰዉ በመስታዉት ፋብሪካዉ መጋዘን ዉስጥ ተከማችቶ የነበረዉ መጠኑ ሰባት ኮንቴኔር የሚያህልና ለሽያጭ የተዘጋጀ መስታወት በመደርመሱ ነዉ።

ህይወቱ ያለፈዉ የ52 ዓመት ሰዉና ጉዳት የደረሰበት 25 ዓመት ሰዉ የፋብሪካዉ ሰራተኞች ሲሆኑ አደጋዉ በደረሰበት ወቅት በመጋዘኑ ዉስጥ በስራ ላይ እንደነበሩ ተጠቁሟል።

በአደጋው ሰፍራ የተገኙት የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተደረመሰዉን ከፍተኛ መጠን ያለዉ መስታወት በማንሳት ጉዳት የደረሰበትን ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል ያደረሱ ሲሆን ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን ከፍርስራሹ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር አራት ሰዓት ፈጅቷል ሲሉ አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news