Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ኤልያስ ሁለት ገዳማት ከጥር ወር ጀምሮ ንጹሃን መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ! የኢትዮጵያ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በደብረ ኤልያስ ሁለት ገዳማት ከጥር ወር ጀምሮ ንጹሃን መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ግንቦት 28፤ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሦስት ክልሎችን ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁኔታ አሳውቋል። 

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በሁለት ገዳማት "በአካባቢዉ የታጠቀ ቡድን እየሰለጠነ ነዉ" በሚል ከጥር 22፤ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በነበረ ግጭት በንጹሃን ላይ ግድያና የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጿል።

በብሄረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ስላሴ እና ተክለ ኃይማኖት ገዳማት ከግንቦት 18፤ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መከፈቱን አስታውቋል። በዚህም የአካባቢዉ አርሶ አደሮች በሰላም የግብርና ስራቸዉን ለመስራት እንደተቸገሩ እና የገዳማቱ መናኝ መነኩሴዎችም ላይ የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን ገልጿል።እንዲሁም ግጭቱን በሸሹ ሰዎች ላይ "ተምቻ" በተባለ ወንዝ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እየሆኑ ነው ሲል ኢሰመጉ ከአካባቢው አሰባሰብኩ ካለው መረጃዎች ተረድቻለሁ ብሏል።

መንግስት ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ በአካባቢው መሸጉ ያላችው ኃይሎች ትጥቅ ትግል ለማድግ ሲንቀሳቀሱ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።ከአምስት የጸጥታና ደህንነት ተቋማት የተውጣጣው ግብረ ኃይል "በእስክንድር ነጋ" ይመራል ያለው ቡድን "መንግስትን ለመጣል" እቅድ እንዳለው ገልጿል። ተወሰደ በተባለው እርምጃም 200 ታጣቂዎች መገደላቸውን ተናግሯል።

የታጣቂ ቡድኑን መሪና ግብረአበሮች እያሳደደ መሆኑን የገለጸው መንግስት፤ ስለ ንጹሃን ጉዳት ያለው ነገር የለም። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የፌደራሉ መንግስት ወደ አማራ ክልል ያሰገባውን ሰራዊት እንዲያስወጣ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news