Get Mystery Box with random crypto!

በኮሪደር ልማት 1 ሺህ 135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸዉን የአዲስ አበባ ከ | ETHIO-MEREJA®

በኮሪደር ልማት 1 ሺህ 135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ተናገሩ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸዉ አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም ብለዋል

በትናንትናው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጥያቄ ካቀረቡ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፤ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች መካከል “1,135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸውን” በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል።

“1,135 ሰው ማለት ቀላል አይደለም። በዚህ ወቅት፣ በዚህ የኑሮ ውድነት፣ በዚህ ጊዜ ተረጋግቶ የሚኖርበት አጋጣሚ ካልተፈጠረ፤ የሚሰራውን ስራ ሁሉ በዜሮ ድምር የሚያባዛ ነው የሚሆነውና እርሱ ለምን ግምት ውስጥ አልገባም?” ሲሉ መጠየቃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ90 ቀናት እንዲጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘለት በመጥቀስም፤ “የግድ በዚህ ሶስት ወር ውስጥ ስራ ማለቅ አለበት ወይ?” ሲሉ ተጨማሪ ጥያቄ አስከትለዋል። “በጊዜ ተለክቶ ስራ መሰራት አለበት፤ ልክ ነው። አምናም የ90 ቀን እቅድ ተብሎ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል። ሁልጊዜ ግን በዚህ መልክ በዘመቻ መሰራት አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ ይስነሳል” ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ “ነገሮች በተረጋጋ እና በታቀደ መልኩ እንዲሄዱ ለማድረግ መሰራት የለበትም ወይ?” ሲሉ አስተያየት አዘል ጥያቄ ማንሳታቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የምክር ቤት አባሉ ከጠቀሷቸው የልማት ተነሺዎች ውስጥ “አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም።

     T.me/ethio_mereja
       @ethio_mereja