Get Mystery Box with random crypto!

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የፕሪቶሪያው ስምምነት 'እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር' ጠየቁ | ETHIO-MEREJA®

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የፕሪቶሪያው ስምምነት "እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር" ጠየቁ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር “በአካባቢው ማህበረሰቦች መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በጥልቀት እየተከታተሉ” መሆኑን ገልጸው፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት “እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር” ጥሪ አቀረቡ።

የህብረቱ ሊቀመንበር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፤  ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት “በጣም አዋጭ አካሄድ”  የሆነው “የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ ያቀረቡ” ሲሆን በህወሃት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ  የተደረሰው የሰላም ስምምነት “እንዲከበር እና ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ጠይቀዋል።