Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን ከ200 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወነጨፈች ለሊቱን ኢራን ከ200 በላይ ገዳይ ድ | ETHIO-MEREJA®

ኢራን ከ200 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወነጨፈች

ለሊቱን ኢራን ከ200 በላይ ገዳይ ድሮኖች፣ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ስታስወነጭፍ ማደሯ ተሰምቷል፡፡

ጥቃቱ ከቀናት በፊት በኢራን ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ከፍተኛ የኢራን ጄኔራልን ጨምሮ 13 ሰዎች በመገደላቸው የበቀል እርምጃ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ለሊቱን የእስራኤል ጦር በሰጠው መግለጫ ኢራን ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ውስጥ አብዛኛውን ማክሸፍ ተችሏል ተብሏል፡፡ ወታደሮች በሁሉም ግንባሮች ተሰማርተውና ተዘጋጅተው የእስራኤልን ግዛት መከላከላቸውን ይቀጥላሉ ሲሉም አስታውቋል፡፡
 
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የኢራንን ጥቃት የመከላከል እርምጃዋን እንደምትቀጥል አስገንዝበው የማጥቃት ምላሽ እንደሚሰጡም ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቢሆኑም ለእስራኤል ያላቸውን ቁርጠኛ ድጋፍ ገልጸው የጂ7 አገራት ቡድን መሪዎችን አስቸኳይ ስብሰባ እንዲቀመጡ ጠይቀዋል፡፡ ይህም የተባበረ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ለማስተባበር እንደሆነ የኤን ዲቲቪ ዘገባ አመላክቷል፡፡ እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ሜክሲኮ፣ እና ኔዘርላንድ ያሉ መሰል  የአውሮፓ ሀገራትም የኢራንን ጥቃት አውግዘዋል። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አስመልክቶ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja