Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ኃይል መላኳን አስታወቀች። አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ | ETHIO-MEREJA®

አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ኃይል መላኳን አስታወቀች።

አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ኃይል መላኳን ያስታወቀችው ኢራን በእስራኤል ላይ የበቀል ጥቃት ታደርጋለች የሚለው ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተባለው ጥቃት በሶሪያ የሚገኘው የኢራን ኢምባሲ መመታቱን ተከትሎ ኢራን እንደምትበቀል በተጋጋሚ ዝታለች።

በዚህ ጥቃት ከፍተኛ የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ አባል የሆነ ወታራዊ ባለስልጣንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ተገድዋል።የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ባለፈው የረመዳን ፆም ማብቂያ ላይ እንደተናገሩት ጥቃት አድራሿ እስራኤል መቀጣት አለባት የሚል ዛቻ ማሰማታቸው ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢራን ይደገፉል የሚባለው የሊባኖሱ ታጣቂ ሂዝቦላም፣እሰራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ አድርሳዋለች ላለው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የእስራኤልን የከባድ መሳሪያ ይዞታዎች ኢላማ ማድረጉን ገልጿል።የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሜሪካ በእስራኤል ጥቃት መሰንዘሯ የማይቀር ነው ሲሉ በትናንትናው እለት አስጠንቅቀዋል።እስራኤል፣ ኢራን ልትቃጣው ለምትችለው ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

የእስራኤል እና የኢራን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ወትሮውንም መልካም የሚባል ባይሆንም፣ ከደማስቆው የኢምባሲ ጥቃት በኋላ ወደ ከፋ ደረጃ ደርሷል።

   - ETHIO-MEREJA -
   
T.me/ethio_mereja