Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናመረጃ 10 አስገራሚ የአቮካዶ የጤና ጥቅሞች!! አቮካዶን መመገብ ከሚያስገኛቸው ብዙ ጥቅሞች | ETHIO-MEREJA®

#ጤናመረጃ

10 አስገራሚ የአቮካዶ የጤና ጥቅሞች!!

አቮካዶን መመገብ ከሚያስገኛቸው ብዙ ጥቅሞች ዋነኞቹን እናያለን።

1) አቮካዶ የደም ግፊትንና የደም ዝውውርን የሚያስተካክለውን ፖታሲየም የተሰኝውን ንጥረ ነገር በብዛት ይዟል፡፡ ይህ ፖታሲየምም ሙዝ ውስጥ ከሚገኝው በ10% ይበልጣል።

2) አቮካዶ ፎሌት የተባለ ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚና ለህፃኑ የአእምሮና አካላት እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት የሚመጣውን ማቅለሽለሽ የሚከላከል ቫይታሚን ቢ6 ይዟል።

3) በአቮካዶ ውስጥ ያለው ሞኖሳቹሬትድ ፋት ለልብ ህመም የሚያጋልጠንን ኮሌስትሮል በመቀነስ ጤናን ያስተካክላል።በተጨማሪም ለስኳር በሸተኞች በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ በመቀነስ ይጠቅማል።

4) አቮካዶ ኦሊይክ አሲድ በውስጡ ይዟል። ይህ አሲድ የጡት ካንሰርን ይከላከልልናል።

5) አቮካዶ ሊየቲን የተባለ ቫይታሚን ሲኖረው ይህ ቫይታሚን የካሮቲን ቫይታሚን ከሆነው ቫይታሚን ኤ ዝርያ የሚመደብ ሲሆን ለአይን ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።

6) አቮካዶ ከፕሮስቴት ካንሰር የሚከላከሉና የተጐድ ሴሎችን የሚጠግኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ይዟል።

7) አቮካዶ የአፍ ካንሰርን ከመከላከሉ ባሻገር ለመጥፎ የአፍ ጠረን አይነተኛ መፍትሄ ነው።

8) በአቮካዶ ውስጥ ያሉት ኢንዛይምና የምግብ ንጥረ ነገሮች የተጐዳ የጨጓራና የትንሽ አንጀት ግድግዳዎችን በማለስለስ ወደር አይገኝላቸውም።

9) በአንቲ ኦክሲዳንት የበለፀገ ስለሆነ ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ምልክቶችን ይከላከላል።ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል የነርቭ ስርዓት ጤናማ እንዲሆን ያደርል።

10) በቫይታሚን የበለፀገ ሲሆን ቆዳችንን ከፍሪራዲካልስ ይከላከላል።

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
@ethio_mereja