ተጠናቀቀ ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን ሆኗል ! የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንሳይ ርዕሰ መዲና ፓሪስ በሚገኘው ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ሲካሄድ ሪያል ማድሪድ ከ ሊቨርፑል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 - 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግብ ቪኒሰስ ጁኒየር አስቆጥሯል። ሪያል ማድሪድ ለአስራ አራተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ። ቪኒሰስ ጁኒየር በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ግብ ያስቆጠረ አምስተኛው በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ሆኗል። ቪኒሰስ ጁኒየር በዘንድሮ የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በአስር ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን አድርጓል ። ሊቨርፑል 0 - 1 ሪያል ማድሪድ ቪኒስየስ ጁኒየር 59 T.me/ethio_mereja @ethio_mereja 2.9K viewsedited 21:36