Get Mystery Box with random crypto!

የ20 21/22 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ዛሬ ምሽት በፓርክ ደ ፍራንስ ፓሪስ ፍፃሜውን ያገኛ | ETHIO-MEREJA®

የ20 21/22 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ዛሬ ምሽት በፓርክ ደ ፍራንስ ፓሪስ ፍፃሜውን ያገኛል።

የዓመቱ አውሮጳ እግር ኳስ ሻምፒና የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ይካሄዳል። ፓሪስ የተቀናቃኞቹን የስፔኑን ሪያል ማድሪድ እና የእንግሊዙን ሊቨርፑል ክለቦች ደጋፊዎች ተቀብላ የጫወታው መጀመር እየተጠበቀ ነው።

-የመድረኩ ልዕለ ሃያል የ13 ጊዜ የመድረኩ ሻምፒዮን የሆነው የጋላክቲኮ ስብስብ ሪያል ማድሪድ ከሌላኛው በመድረኩ የ6 ጊዜ ባለ ድል የእንግሊዙ ሃያል ክለብ ሊቨርፑል ጋር ይፋለማሉ።

ዘንድሮ ሪያል ማድሪድ በካሪም ቤንዜማ፣ በወጣቶቹ ቭንሽየስ ጁኒየርና ሮድሪጎ፤ በመሃል ሜዳ ተክኒሻን ሉካ ሞድሪች ጥምረት፤ ከአንድም ሁለቴ ሞቶ እየተነሳ ፒ ኤስ ጂ፣ ቼልሲንና ማን ሲቲን አሰናብቶ ለአሥራ አራተኛ ድል ፓሪስ ይገኛል።

ቀያዮቹ ዘንድሮ በቆፍጣናው የታክቲክ ሊቅ የርገን ክሎፕ እየተመራ በቫይዳይክ ድንበሩን አስከብሮ፤ በሞሳላህና በሳይዶ ማኔ ድንቅ ብቃት ታግዞ ለዋታው ይቀርባል። ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀድመው የካራባኦና የኤፍ ኤ ዋንጫ በማንሳት በተሻለ ጥንካሬ ላይ የሚገኙ ሲሆን ይህን ዋንጫ በቀላሉ ለማድሪድ ይሰጣሉ ተብሎ አይገመትም ።

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 4:00 ይደረጋል ።

ማን ያሸንፋል ? ይገምቱ!

T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja