Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ!! ኮሚሽኑ | ETHIO-MEREJA®

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ!!

ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበው መንግሥት የሚያስራቸው ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ በሔደበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ በሥራው ምክንያት የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም ሲሉ ለጋዜጠኞች መብት ለሚሟገተው ሲፒጄ ተናግረዋል። ኃላፊው ትላንት አርብ ከሲፒጄ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የታሰሩት ፖሊስ ወንጀል ለመፈጸማቸው ማስረጃ በማግኘቱ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ከሚዲያ ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል ለሚባሉ ወንጀሎች የቅድመ-ዳኝነት እስርን እንደሚከለክል የጠቀሱት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ" የታሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ሁሉ ሊፈቱ ይገባል" የሚል ጥሪ ዛሬ ቅዳሜ አቅርበዋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja