Get Mystery Box with random crypto!

ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ሩሲያ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀመረች!! | ETHIO-MEREJA®

ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ሩሲያ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀመረች!!


የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጊ ሾይጉ በሰጡት አስተያየት፤ ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸው በሩሲያ ድንበር አካባቢ ወታደራዊ ስጋቶች እንዲጨምሩ ያደርጋል ብለዋል። ይህንን ተከትሎም ሩሲያ አስፈላጊ የሆኑ የአፀፋ እርምጃዎችን መውሰድ እንደጀመረች መግለጻቸውን ኢንትራፋክስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

በዚህም ሩሲያ በምእራብ ወታደራዊ ቀጠና ላይ ተጨማሪ 12 የጦር እዞችን በማቋቋም ምለሽ እንደምትስጥም ነው የመከላከያ ሚኒስትሩ ያስታወቁት። ፊንላንድ እና ሰዊድን ባለፍነው ረቡዕ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል በይፋ ማመልከታቸው ይታወሳል።

ፊንላንድ እና ስዊድን ውሳኔ ተከትሎ በኋላም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፒቲን በሰጡት አስታያት ሀገራቱ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ቢቀላቀሉም ለሀገራቸው ስጋት እንደማይሆን ገልጸዋል። ፑቲን ሁለቱ ሀገራት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ለሩሲያ ስጋት ባይሆንም ምላሽ ሊያሰጥ እንደሚችል መናገራቸውም ይታወሳል። የፖለቲካ ሰዎች የስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል አሁን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ወደ ሌሎች ሀገራት ሊያዛምተው እንደሚችል እየተነበዩ ነው።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮመረጃ