Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ምሽት ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ይታያል!! በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች ዛሬ ምሽት እና ነገ ማ | ETHIO-MEREJA®

ዛሬ ምሽት ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ይታያል!!

በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች ዛሬ ምሽት እና ነገ ማለዳ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ እንደሚታይ ቢቢሲ ዘግቧል።

ከግርዶሹ ደቂቃዎች በፊት ጨረቃ ብርቱካናማ ቀይ መልክ ይዛ ወይንም “ደም ለብሳ” የምትታይ ሲሆን ክስተቱ ከፕላኔታችን አስደናቂ እይታዎች አንዱ የሆነው የጨረቃ ግርዶሽ በሰማይ ላይ ይሆናልም ተብሏል።

ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ የሚፈጠረው ምድር በፀሐይ እና በጨረቃ መካከል በምትሆንበት ጊዜ የሚከሰት ነው።

ክስተቱ በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ አገራት ሰኞ ማለዳ እንደሚታይ የሚጠበቅ ሲሆን በአሜሪካ ደግሞ በአንፃሩ ዛሬ እሁድ ምሽት ላይ ያያሉ ነው የተባለው።

ጨረቃ ከምህዋሯ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ ላይ እንደምትሆንና ከወትሮው በበለጠ ተልቃና ገዝፋ እንደምትታይም ይጠበቃል ተብሏል። በመሆኑም ማንኛውም ሰው የጨረቃ ግርዶሹን ክስተት በዓይን ማየት የሚችል ሲሆን አቅርቦ ማሳያ (ባይኔኩላር) ወይም አነስተኛ ቴሌስኮፕ በመጠቀምም የሚፈጠረውን የቀይ ቀለም የበለጠ ለማየት ይችላል ነው የተባለው።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ