Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ኢሰመኮ አሳሰበ!! የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌ | ETHIO-MEREJA®

በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ኢሰመኮ አሳሰበ!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል። ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።

ጦርነቱ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ እንግልት እንዲዳረጉ፣ የሚወዷቸውን ሰዎች እንዲያጡ፣ ህይወታቸውን በእርዳታ ላይ እንዲመሰረቱ፣ መሰረታዊ የዜጎች አገልግሎቶችን እንዲነፈጉ እና የሌሎችን ጉዳቶችን እያስተናገዱ እንደሚገኙም ተቋሙ ከዚህ በፊት ባደረኳቸው ተደጋጋሚ ምርመራዎች አረጋግጫለሁ ብሏል።

የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የሰሜን ኢትዮጵያ ሶስቱ ክልሎች ዋነኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ያለምንም ገደብ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ ማድረግ እንደነበርም ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት የምርት እጥረቶች እና የዋጋ መናር ተከስቶ ዜጎች በአስከፊ ሁኔታ ህይወታቸውን እንዲገፉ ተገደዋል ያለው ኢሰመኮ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ መፈለግ ይገባል ብሏል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ወይም ኢጋድ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኢሰመኮ አሳስቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ