Get Mystery Box with random crypto!

የገርጂ ዘመናዊ መኖሪያ መንደር በተለያዩ አካላት ተጎበኘ!! በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው እና የአል | ETHIO-MEREJA®

የገርጂ ዘመናዊ መኖሪያ መንደር በተለያዩ አካላት ተጎበኘ!!

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው እና የአልሙኒየም ፎርምወርክ የግንባታ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደርን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር) እና ባለሀብቱ ነጅብ አባቢያ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ኮርፖሬሽኑ በግንባታ ቴክኖሎጂ እና አስተዳደር እያሳየ ባለው የላቀ አፈጻጸም የመኖሪያ መንደሩን በ18 ወራት ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ መቃረቡ ተገልጿል።

ይህም በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ጥራትን፣ ቅልጥፍና እንዲሁም ዘመናዊነትን አጣምሮ እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ መንደር በአጭር ጊዜ መገንባት መቻሉ ኮርፖሬሽኑ ብቃት ባላቸው እና የፕሮጀክት አስተዳደር እውቀት ባካበቱ አመራሮች እየተመራ መሆኑን ማሳያ መሆኑን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ