Get Mystery Box with random crypto!

በደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ የገበታ ለሀገር | ETHIO-MEREJA®

በደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው የደንዲ ሃይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 127 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ደንዲ ሃይቅ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጅ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የጣልያኑ "ዊ ቢውልድ" ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔትሮ ሳሊኒ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የወንጪ ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት አስተባባሪና የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ