Get Mystery Box with random crypto!

የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!! ባሳለፍነው ሳምንት 131 ሚሊየን 481 ሺሕ | ETHIO-MEREJA®

የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!

ባሳለፍነው ሳምንት 131 ሚሊየን 481 ሺሕ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል 40 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 90 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዛቸውን ነው የገለጸው፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሲሆን በቅደም ተከተላቸው 14 ነጥብ 7 ሚሊየን፣ 9 ነጥብ 7 ሚሊየን እና 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸው ተገልጿል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ኅብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 15 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ሥራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የክልልና የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ሕዝብ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ