Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ የክብ | ETHIO-MEREJA®

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ የክብር ዶክትሬት ሰጠ!!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርሃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በልማትና ሌሎችም ተግባራት የላቀ ሚና የተወጡ ናቸው ተብሏል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ 8ኛው ፕሬዚዳንት በመሆን እየመሩ ያሉት አዴሲና በአህጉሪቷ የድህነት ቅናሳ፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የስራ ፈጠራ እና ሌሎችም ተግባራት ላይ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸው ይታወቃል።

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲቪል ስራዎች ግንባታ ስኬታማነት ኃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ናቸው። ኢዜአ እንደዘገበዉ በግድቡ ግንባታ ስኬት የላቀ ሚና ለነበራቸው ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ