Get Mystery Box with random crypto!

#ምትኬ ክፍል-16 #ደራሲ_HiLA ዛሬ ሰናይትን ወደ ቤት አመጣታለሁ ብሩኬ አስፈላጊውን ሁ | ኢትዮ-ልቦለድ & ❤️❤️📚

#ምትኬ

ክፍል-16

#ደራሲ_HiLA

ዛሬ ሰናይትን ወደ ቤት አመጣታለሁ
ብሩኬ አስፈላጊውን ሁሉ ከከፈለ በኋላ መውጫ አፅፎ ተያይዘን ወደ መኪና ገባን እንደው ድንገት ዞር ስል ሰናይትን በደንብ አስተዋልኳት የዋህ መሳይ ፊት አላት ዝም ያለች ናት መልሶቿ ቁጥብና ቀዝቃዛ ናት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፏን ገፇ ይመሰክራል እሷ ግን እንደው ጥንካሬውን አድሏታል መልኳ በዚ ሁሉ ውስጥ አልፋ እንኳን ቆንጆ ናት ያውም ጠይም አይኗ ከንጣቱ ትልቅነቱ ገና ሲያዩት ያስደነብራል ፀጉሯ ረጅም ባይሆንም ልክ እንደኑግ የጠቆረ ነው ሰውነቷ ደንደን ብሎ ሞላ ያለ ነው በአጠቃላይ የደስደስ ያላት ወጣት ናት ትንሿ ልጇ ከመዳፍም እምታልፍ አትመስልም እንደው ግን ባልተገለጡት አይኖቿ ባልተዘረጉት ጣቶቿ ፍቅር ታሲዛለች ሲያይዋት ውለው ቢያድሩ አሰለችም ትንሽዬ መልአክ ትመስላለች የሆነ የአምላክ አገልጋይ አይነት ምትሀት አላት በቃ አቅፌ ስይዛት ጠረኗ መአዛዋ ልክ የመቅደሱን እጣን አለኝ ንፁህ ያልጎደፈ እንዳው እሚያውድ የሆነ ሀይልማ ተሰጥቷታል ፈዝዤ እያየኀት እጇን እየሳምኩ ቤት ደረስን በቃ እናቴ እልል ብላ ተቀበለችን ሁሌም እሚገርመኝ ብሩኬ ቀና ብሎ አይኗን ማየት ይፈራል እማዬም ስለምታቅ እስኩ እስኪሄድ ዞር ትላለች፡፡
በቃ በደንብ ተቀበለችን ከሰናይት ጋር አስተዋወኳት ሁሉን አሟልታ ነበር የጠበቀችን ወይኔ እናቴ ፍቅር እኮ ናት እንደ በሀላችን አናቷን በቂቤ አንጀቷን በአጥሚት ትጠግነው ገባች ትንሽ አውርቻት ለእረፍት ገባሁ እማዬ የልጅቷን ስም ስጠይቃት ሴና መሆኑን ነገረቻት በጣም ስለገረመኝ ተመልሼ ለምን እንዳለቻት እና ትርጉሙን ጠየኳት
"ሴና ማለት በኤሮምኛ ታሪክ ማለት ነው ልጄ ታሪኬ በሷላይ ብዙ ታሪኮቼን መዝግቤ ይዣለሁ አይናን ሳየው ማንነቴን አስታውሳለሁ የትላንት ታሪኬን በሷ ገፅ ላይ ማንም ሊያነበው ይችላል እኔን ለማወቅ ሴናዬን ማየት በቂ ነው፡"
እውነቷን ነው የሁሉም እናቶች ታሪክ በልጆቻቸው ገፅ ይመሰከራል የነሱ መራብ ለኛ የጥጋብ መንስኤ ነው የነሱ መጎሳቆል የነሱ ሀዘን የነሱ የተመሰቃቀለ ህይወት ለኛ ነው ታሪካቸውን በኛ ለመፃፍ እኛን ለማኖር እናትነት ያልተገለጠ ገና ያልገባን ታሪክ ነው ሁላችንም የነሱ ሴና ነን፡፡
* * *
ቀኖች እርስ በእርስ እየተዋለዱ ወራትን ተኩ እነሆ ሰናይት ከወለደች ሁለት ከአስራአምስት ቀን ሆናት ልጇ ሴናም ክርስትና ልትነሳ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተዋታል፡፡ እማዬም ሽርጉዱን ተያይዛዋለች የሰፈር ሰው ሁሉ የኛ ዘመድ እንደሆነች ነው ሚያቀው ፡፡ ብሩክና እማዬም ጥሩ ወዳጆች ሆነዋል ቤት ሲመላለስ እንደበፊቱ አይፈራም፡፡ እኔም ስራዬን በሚገባ ሁኔታ ወድጄውም ለምጄውም ነው እየሰራሁ ያለሁት የብሩኬ እናት ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለች አንዳዴ እማዬ ጋር ትመጣ እና አምሽታ ተጫውታ ትሄዳለች፡፡ ብቻ ፈጣሪ ይመስገን ጥሩ ቤተሰባዊ ቅርበት አለን፡፡
የሴናዬ የኔ ልዕልት ክርስትናዋ ነገ ነው አጥቢያችን ከሆነው ቅዱስ ገብርኤል ቤተከርስቲያን ነው የምናስነሳት ብለናል ሰናይትም እኔ ክርስትና እናቷ እንድሆን ስጠይቀኝ እኔም ብሩኬም እማም ሁላችንም ነበር ደስተኛ የሆነው ሴና ፍቅር የሆነች ትንሽዬ ልዕልት ናት፡፡ በለሊት ሄደን የቤተክርስቲያኑን ስነስርዓት ካጠናቀቅን በኋላ ወደቤት ተመለሰን እናቴ ሁሉን አዘጋጅታ ስለነበር ጥሩ ድግስ አርጋ ጠበቀችን ሁላችንም በደስታ ነበር ያሳለፍነው ሲበላ ሲጠጣ አመሸን ብሩኬና እናቱ አምሽተው ሄዱ ቤትዬም ከእኔ ጋር አደረች፡፡
ነገሮች በመልካም መሄድ ቀጥለዋል ሰናይትም እናቴን እያገዘች ልጇን እያሳደገች ነው ሴናዬም እምታሳሳ እንቁ እየሆነች ነው፡፡ ብሩኬ እና ቤቲ ከኔ በላይ ከሴና ፍቅርም ሱስም ይዟቸዋል በየቀኑ ሳያዩአት አያድሩም፡፡ ሴናዬ እያደገች ሰናይትም እየተላመደች በመጣችበት ወቅት አንድ ቀን ጠዋት ሴና አምርራ ማልቀስ ጀመረች እኔ እና እማዬ ተሯሩጠን ወደ ክፍሉ ስንገባ ግን ባየነው ነገር ደነገጥን በህልሜም መሰለኝ አልተኛሁም ብቻ ደነዝኩ ከድንዛዜዬ ያነቃኝ የልጄ ሴና ለቅሶ ነበር፡፡