Get Mystery Box with random crypto!

[ Album ] #MekdelaAmbaUniversity መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አ | Ethio Job Vacancy

[ Album ]
#MekdelaAmbaUniversity

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

የሥራ መደብ ➧ ፕሬዝዳንት (የዩኒቨርሲቲውን ሥራዎችን በኃላፊነት ይሰራል፣ይመራል)

የትምህርት ደረጃ ➧ 3ኛ ዲግሪ ወይም 2ኛ ዲግሪ እና ቢያንስ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ

የሥራ ልምድ ➧ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም በሌላ መስክ ለሥራ መደቡ አግባብነት ባለው የተረጋገጠ የአመራርነት፣ የኃላፊነት እንዲሁም የምርምርና የማስተማር ልምድ ያለው/ያላት

አጭር ስትራቴጂክ ፕላን ➧ አመልካቾች የሚወዳደሩበትን ዘርፍ ዋና ተግባር ለማሳደግና ለማሻሻል ስለሚከተሉት ስልት ከ10 ገጽ ያልበሰ አጭር መግለጫ በፅሁፍ ያቀርባሉ

የሥራ ዘመን ➧ በውድድሩ የላቀ ውጤት በማምጣት የተመረጠው/ችው አመልካች በፕሬዝዳንትነት ለስድስት ዓመታት የሚሾም/የምትሾም ይሆናል

አመልካቾች CV፣ የትምህርትና የሥራ ልምድ እና ሌሎች ማስረጃዎችን ዋናውን ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ እንዲሁም 10 ገፅ አጭር መግለጫ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ጽ/ቤት ወይም ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ ወይም በኢሜይል መላክ ይችላሉ፡፡

የማመልከቻ ጊዜው የፊታችን አርብ መጋቢት 08/2015 ዓ.ም ያበቃል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

+251914074314 / +251914060672

(ሙሉ የማስታወቂያው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@ethio_job_vacancy
@ethio_job_vacancy