Get Mystery Box with random crypto!

'ማንኛውም ት/ቤት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ሀገራዊም ሆነ የዜግነት ግዴታ | የእውቀት ማህደር

"ማንኛውም ት/ቤት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ሀገራዊም ሆነ የዜግነት ግዴታ አለበት" - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለሁሉም የዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለ3ቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት/መምሪያዎች በላከው ደብዳቤ ት/ቤቶች ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን እንዲያስተናግዱ በጥብቅ አሳስቧል።

ትምህርት ቢሮው፥ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት በክልሉ በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሰ/ወሎ፣ ከዋግኽምራ እና ሰ/ጎንደር ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎች የ2014 ትምህርት ገብተው ለመማር በተለያዩ ት/ቤቶች ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብሏል።

ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ባለመያዛቸው ምክንያት ለከፍተኛ እንግልትና የትምህርት እድል እንዳያገኙ እያደረጋቸው መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

ማንኛውም ትምህርት ቤት የተለያዩ ምክንያቶችን (የክፍል ጥበት አለብኝ፣ መምህር የለኝም ወዘተ) በመደርደር ተፈናቃይ ተማሪዎችን አለመቀበል ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል።

በመሆኑንም የዞን አመረር፣ የወረዳ ት/ፅቤት አመራር እና የት/ቤት ርዕሰ መምህራን በጋራ ተመካክረው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።

ትምህርት ቢሮው፥ማንኛውም ት/ቤት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ ሀገራዊም ሆነ የዜግነት ግዴታ አለበት ያለ ሲሆን መረጃ ማቅረብ የማይችሉ ተማሪዎች ካሉ ተማሪው ደርሸበታለሁ ባለው የክፍል ደረጃ በማመልከቻ ት/ቤቱ በሚያዘጋጀው ፎርም ላይ በማስሞላት እና በማስፈረም እንዲገቡ እንዲደረግ በጥብቅ አሳስቧል።
Via Tikvah

#share & #join

@ETHIO_IQ
Stay Safe!