Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ሶስት የተለያዩ የቴሌ ብር የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይ | Afrihealth TV

ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ሶስት የተለያዩ የቴሌ ብር የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአንድ አመት በፊት ይፋ ባደረገው የቴሌ ብር የፋይናንስ አገልግሎት ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከ55 በላይ ተቋማት ጋር ቴሌ ብር እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬ ህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ዛሬ ይፋ የተደረጉት የፋይናንስ አገልግሎቶች ሶስት ሲሆኑ እነዚህም፦ቴሌ ብር እንደ ኪሴ፣ቴሌ ብር መላ እና ቴሌ ብር ሳንዱቅ/ቁጠባ ናቸው።

ቴሌ ብር መላ/ብድር፦ ለግለሰብ እስከ 10,000 ብር ለተቋማት ደግሞ እስከ 100,000 ሺህ ብር የብድር አገልግሎት ይሰጣል።

ቴሌ ብር እንደ ኪሴ፦ በቴሌ ብር አማካኝነት ግብይት ሲፈፀም የጎደለ የገንዘብ መጠን ካለ እስከ 2,000 ብር የብድር አገልግሎት ይሰጣል።

ቴሌ ብር ሳንዱቅ/ቁጠባ፦ ከትንንሽ ገንዘቦች ጀምሮ መቆጠብ የሚያስችል የፋይናንስ አገልግሎት።

ብድሩ በዳሽን ባንክ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ሲስተሙ ደግሞ በኢትዮ ቴሌኮም የሚመራ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የዚህ የፋይናንስ አገልግሎት ለማስጀመር ያስፈለገበት ምክንያት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።