Get Mystery Box with random crypto!

የቀጣይ ዓመቱ የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ፕ | Afrihealth TV

የቀጣይ ዓመቱ የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2015 የጨዋታ መርሃ ግብርን ዛሬ ረፋድ በጽህፈት ቤቱ አውጥቷል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከመውረድ የተረፉ 13 ክለቦችና ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ኢትዮጵያ መድህንና ኢትዮ ኤሌክትሪክን አካቶ የ16ቱን ክለቦችን የጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ አውጥቷል፡፡
መስከረም 20 2015 የቀጣይ ዓመቱ የፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብር ይጀመራል ያለው አክሲዮን ማህበሩ የመጀመሪያ ዙር የ15 ሳምንት ጨዋታዎቹን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረት በአንደኛ ሳምንት ባህርዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ፣ወልቂጤ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ሃዋሳ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ መቻል ከሃድያ ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ መድህን ከቅዱስ ጊዮርጊስና ድሬደዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና እንደሚጫወቱ የወጣው ድልድል ይጠቁማል፡፡

በመጀመሪያ ዙር ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል በአምስተኛ ሳምንት በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና 6ኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የ2014 የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሳይቆራረጥ መካሄዱን በጥንካሬ በየቀኑ ሶስት ጨዋታዎች ማካሄድን በድክመት ያነሱት የአክሲዮን ማህበሩ የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢው ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ ናቸው፡፡

የ2015 የውድድር መርሃ ግብር ካለፉ ስህተቶች ትምህርት የሚቀሰምበት ነው ያሉት ሰብሳቢው ለተግባራዊነቱ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡