ኢትዮ ቴሌኮም የመጨረሻውን ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ:: አፍሪ ኸልዝ ቲቪ ግንቦት 01/09/2014 ኢትዮ ቴሌኮም የመጨረሻውን ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ይፋ አድርጓል:: በአሁኑ ሰዐት በሸራተን አዲስ ሆቴል ይፋ እየተደረገ የሚገኘው ይህ የሞባይል ቴክኖሎጂ በአለም 70 ሀገራት በአፍሪካ ደግሞ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ6 ሀገራት ተግባራዊ መደረጉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬ ህይወት ታምሩ ተናግረዋል:: በቀጣይ 12 ወራትም 150 አካባቢዎች የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ስራ አስፈፃሚዋ አክለዋል:: 5G ቴክኖሎጂ ማስጀመሪያ ስነ ስርዐቱ ላይ በርካታ ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል:: ዘጋቢ : አክረም ኑርያ 769 views15:46