Get Mystery Box with random crypto!

#ርዕስ: ንገሯት #ግጥም: ሳሚ (Channel Admin) ደሞዜን አውጥቼ ዛሬ ከባንክ ቤት ልሸ | ልብወለድ Ethio_Fiction

#ርዕስ: ንገሯት

#ግጥም: ሳሚ (Channel Admin)

ደሞዜን አውጥቼ ዛሬ ከባንክ ቤት
ልሸምት ዘለቅኩኝ ጤፉን ከወፍጮ ቤት
ሚስቴ ሰው ቤት ሰርታ በሰበሰበችው
ለአትክልት ጥራጥሬ ገበያ ገባችው
.
.
ከወፍጮ ቤቱ በር ዘራፊ ጠብቆ
ይዞ ፈትለክ አለ ገንዘቤን መንጥቆ
ላጠፋ ነውና ራሴን በራሴ
ምንም የለምና የያዝኩት በኪሴ
.
ንገሯት ለሚስቴ
የጤፉን ብር ጥሎ ባልሽ ሞቷል በሏት
ከኔ መሞት በላይ
የጤፉ ገንዘብ ነው እሷን ሚያስለቅሳት::

Comment            Share
    ➷                          ➷
@sam_lizu       @ethio_fiction