Get Mystery Box with random crypto!

በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የህጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900 የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው ተ | Ethio Enterance Preparation

በ18 ሺህ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ የህጋዊነት ማረጋገጫ ተደርጎ 900 የሚሆኑት ሐሰተኛ ሆነው ተገኙ።

የትምህርት ማስረጃዎቹ ተመሳስለው የተሠሩ፣ ዕውቅና ከሌለው ተቋም የተሰጡ፣ ባልተፈቀደ የሙያ መስክ የሰለጠኑ እንዲሁም የመቁረጫ ነጥብና የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው የሠለጠኑ መሆናቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለሥስልጣን አሳውቋል።

የተወሰኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከባለሥልጣኑ ዕውቅና ውጪ ካምፓስ አስፋፍተውና ፍቃድ ባላገኙበት የትምህርት ዘርፍ ስልጠና ሲሰጡ መገኘታቸውንም ባለሥስልጣኑ አረጋግጧል።

ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መርሃ ግብር እና ከተቀመጠላቸው ቁጥር በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ የነበሩ ተቋማት መገኘታቸውንም የባለሥስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልጸዋል።