Construction technologies: ስለ ብሎኬት . Hollow Concret Block (HCB) ወይም የግድግዳ ብሎኬት/Wall HCB/ በመባል ይታወቃል። *የብሎኬት ምርት ሲደረግ ጠቀሜታው ለሁለት ጉዳይ ነው 1. ሸክም መቌቌም የሚችል/Load Bearing/ 2. ሸክም መቌቌም የማይችል /Non-Load Bearing/ *ይሄንን መሰረት ያደረገም የደረጃ ክፍፍል/Class/ ይኖራቸዋል። *ሸክም መቌቌም የሚችሉት ብሎኬቶች "ክላስ ኤ እና ቢ" / Class A and B/ በመባል ሲመደቡ ሸክም መቌቌም የማይችሉት የብሎኬቶች ደግሞ "ክላስ ሲ" /Class C/ በመባል ይመደባሉ። ብሎኬት በተለምዶ በመጠናቸው ባለ10፣ ባለ15 እና ባለ 20 በመባል ይለያሉ:: ርዝመት x ስፋት x ቁመት/ Length x width x depth/ ማለትም Standard Dimenssion *40x20x20cm *40x15x20cm *40x10x20cm እያንዳንዱ ብሎኬት ሸክም የመቌቌም አቅማቸው በሜጋ ፓስካል(Mpa) ይለካል ከዚህ በላይ በምስል አስደግፈናል። *Note: 1 kilogram per square centimetre = 0.0981 mega pascal *Class A=3.8mpa *Class B=3.2mpa *Class C=1.8mpa . ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን። 3.6K views12:02