Get Mystery Box with random crypto!

|| ያለ ሁነኛ አጥቂ አርሰናል ! - ከቅርብ ደቂቃዎች በፊት ታማኙ ለክለባችን ቅርብ የሆነዉ ጆ | ETHIO ARSENAL

|| ያለ ሁነኛ አጥቂ አርሰናል !

- ከቅርብ ደቂቃዎች በፊት ታማኙ ለክለባችን ቅርብ የሆነዉ ጆን ክሮስ አርሰናል ሁነኛ አጥቂ የማስፈረም ዕድሉ ጠባብ ነዉ ሲል ዘግቧል ። ይልቁኑ ካይ ሀቨርትን በዛ ቦታ በማጫወት ወደፊት ተስፋ ያለዉ በቀላሉ የሚገኝ ታዳጊ አጥቂ ይፈልጋል የሚል መረጃን አክሏል ። መጀመሪያ እንዳየሁት ቀልድ ነዉ የመሰለኝ ፤ በእርግጥ የዝዉዉር ጊዜዉ ገና ነዉ ነገር ግን ይሄን ማሰብ ይከብዳል ። በመጀመሪያ ካይ ሀቨርት አጥቂ አይደለም [ false 9 ] በአማርኛ ሀሰተኛ አጥቂ ያ ማለት መስሎ እንጂ ሆኖ የማይጫወት ሲቀጥል ለ ታዳጊ አጥቂ እነ ባሎጉን አይነት የ ሀሌ ኢንድ አጥቂዎች ነበሩ ።

- የሲቲ መንገድ ይመስላል ። ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ቢበላም ትልቁን ዋንጫ ለመሳም እንደ ሀላንድ አይነት ጨካኝ አጥቂ አስፈልጎት ነበር ። እኛ ደግሞ በ ሀሰተኛ አጥቂ ሊጉንም አልበላንም ዋስትናም የለንም ። እርግጥ ነዉ ያለ አጥቂ ብዙ ጎል አግብተናል ነገር ግን አሁንም ሁነኛ አጥቂ ቢኖረን ኖሮ የጣልናቸዉን ነጥብ ባልጣልን ቢያንስ አሁን በ 5 ነጥብ እንርቅ ነበር ብዬ አስባለዉ ። የአምናዉም ዋንጫ ባልባከነ ነበር ። አንድ ቡድን ትልቅ ዋንጫ ለማሳካት ተፈጥሮአዊ አጥቂ ያስፈልገዋል ባይ ነኝ ።

- ቻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደር ክለብ ደግሞ ትልቅ አጥቂ ልዩነት የሚፈጥር ሰዉ ያስፈልገዋል ። በእርግጥ 100 በላይ አዉጥቶ መግዛት ቢከብድም ብዙ አማራጮች ነበሩ ። ነገር ግን መረጃዉ ከገንዘብ አንፃር ሳይሆን ካይ ሀቨርትን እዛ ቦታ ላይ ለማጫወት በማሰብ ነዉ የሚለን ይሄ ይበልጥ አስገራሚ ያደርገዋል ።

"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL