Get Mystery Box with random crypto!

|| ጆሽ ክርኤንኬ የ አርሰናል የስኬት ሚስጥር ! * ዛሬ አንድ ቪዲዮ የፊት ፔጅ ላይ መጣልኝ | ETHIO ARSENAL

|| ጆሽ ክርኤንኬ የ አርሰናል የስኬት ሚስጥር !

* ዛሬ አንድ ቪዲዮ የፊት ፔጅ ላይ መጣልኝ ከዚህ በፊት አይቼዋለዉ ነገር ግን የተቀናበረበት መንገድ እጅግ ልብ ይነካል ። የ All or nothing ቪዲዮ ይመስለኛል ። በአንድ ወቅት አርቴታ እና አርሰናል እጅግ አሰቃቂ የዉጤት ማጣት ዉስጥ በገቡ ወቅት ረጅም ጨዋታዎች ላይ ቀዉስ ገጥሟቸዉ ነበር ። ' Arteta out ' የሚለዉ መፈክር እንደተሰማ ታስታዉሳላቹ ። ታዋቂ የ አርሰናል ዩቱዩበሮች ሳይቀሩ አርቴታ መሰናበት አለበት ሲሉ ይሰማሉ ፣ ደጋፊዎች ከ ጨዋታ በኋላ ቃለ ምልልስ ሲደረግላቸዉ ክለባችንን ገደል ከተተዉ ፣ በህይታችን አርሰናል እንደዚህ ሲሆን አይተን አናዉቅም አርቴታን አስወጡልን አሉ ።

* ሶሻል ሚዲያ ላይ መሸነፍ የበዛባቸዉ ደጋፊዎች ከመናደድ ወደ መሳቅ ተለወጡ ። ' joke club ' የተለያዩ ፖስቶች ይታያሉ ። ተጫዋቾች አንሰራርተዉ የሚጫወቱ አይመስሉም ፣ ስብስቡ ያስቃል ፣ መልበሻ ክፍሉ ሲታይ የ ሀዘን ቤት ይመስላል ፣ የሲቲ ጨዋታ በኢትሀድ 5-0 ስንሸነፍ የደጋፊዉ ፊት ያሳዝናል ። ያኔ ነበር ጆሽ ክሮኤንኬ አርቴታን ለማናገር በ አርሰናል የምግብ መመገቢያ ዉስጥ የጠራዉ ።

- የሚጠበቀው መባረሩ ነዉ ነገር ግን ጆሽ ሰላምታ አቀረበለት እና መረጋጋት እንፈልጋለን አለዉ ። አንድ አንዶች ቡድኑን ለመበጥበጥ ሲነሱ ሳይ ተናድጃለሁ አለዉ ። አርቴታ በምላሹ በሀዘን ፊት እና ድምፅ በጣም ብዙ ልምድ አለህ አለዉ ። ጆሽ ሳቀ ልታምናቸዉ የምትችላቸዉ ብቸኛ ሰዎች ከአንተ ጋር በዚህ ቦታ ያሉትን ነዉ ። ይህን ነዉ የማዉቀዉ ብሎ አለዉ አርቴታ ሲቃ በያዘዉ ድምፅ ይሄን ቃል ለማግኘት ከባድ ነዉ ሲል መለሰለት ። አርቴታ በፈገግታ ተሞላ ።

* ጆሽ በዛዉ ዶክመንተሪ ብቻዉን ቃለ ምልልስ ባደረገበት ወቅት " እኔ እንደማስበዉ ዋናዉ ዓላማችን የዉጪዉን ጩኸት ማስተካከል ነዉ ። አንገታችንን ሳንደፋ እርስበእርስ ጀርባችንን ተደጋግፈን ፤ አንድ ሰዉ ትከሻ ላይ ሌላዉ ክንዱን አሳርፎ ተደጋግፈን መቀጠል ነዉ ሲል ተናገር ። " ይህ ሰዉ የ አባቱ ልጅ አይመስልም ፣ ኳስ ይወዳል ፣ ጨዋታ ይመለከታል ፣ መልበሻ ክፍል ይገባል ፣ ሁሉንም ተጫዋቾች ጋር ያወራል ፣ አርቴታን ይደግፋል በዝዉዉር ይረዳል ። እጅግ የተረጋጋ ሲያወራ ደስ የሚል መሪ ነዉ  ።

- ለዛሬዉ አርቴታ መኖር ትከሻዉ ላይ የመጀመሪያ ክንድ ያስቀመጠዉ ጆሽ ሰላሙ ይብዛ

: @mesutsami12 !

"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL