Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO_ALJEZIRA

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_aljezira — ETHIO_ALJEZIRA E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_aljezira — ETHIO_ALJEZIRA
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_aljezira
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.12K
የሰርጥ መግለጫ

Ehio_aljezira access fact information

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-19 19:40:04
የ 2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ዉጤት መለቀቁ ይታወሳል ፤ ከዉጤቶቻችሁ በመነሳት የተለያዩ ደረጃዎች እና ዳታ Analysis በሁሉም ቦቶቻችን ማቅረብ እንጀምራለን።

ካቀረብንላችሁ መካከል አንዳንዱ የሚከተሉትን ይመስላል፤

የሃገር አቀፍ ደረጃ / national Rank
የት/ቤት ደረጃ / School Rank
ተመሳሳይ ዉጤት / Score Twin
ከዚህ ነጥብ በላይ ስንት ሰው አለ ?
የምደባ ግምቶች
እና የመሳሰሉት!

ያስመዘገባችሁትን ደረጃ ለማየት ወደቦቶቻችን ጎራ ይበሉ።

እዚህ ጠቅ ያድርጉ እና ይጀምሩ

t.me/NeaGovEt_bot?start=r1055112414
544 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 15:58:05
ጉዳዩ፡- የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ይመለከታል

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት አስመልክቶ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጣቸው ማብራሪያ ተሰጥቷል

አዲስ በተጠናው የትምህርትና ሥልጠና ፍንተ-ካርታ መሠረት ቀደም ሲል የሁለተኛ ደረጃ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የነበረው በአዲሱ የትምህርት እርከን መሰረት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል። በዚህ መሠረት ቀደም ሲል 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና 12ኛ ክፍል ማብቂያ ላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ወደፊት የሚሰጠው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መሸፈን ያለበት የትምሀርት ያዘት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለው ምን እንዳለበት፥


የኢኮኖሚክስ ትምህርትን በተመለከተ በ2013 የትምህርት ዘመን የ11ኛና የ12ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ወጥ በሆነ መልኩ እየተሰጠ እንዳልነበር ያሳያል፡፡ በመሆኑም በተሰበሰው መረጃ መሠረት የትምህረቱ አሰጣጥ ወጥነት ሳይኖረው ፈተናውን መስጠት በፈተናው አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሰለሚያሳድር የኢኮኖሚክስ ትምህረት ፈተና #ባይሰጥ የተሻለ መሆኑን ቀደም ሲል በተሰጠው ምክረ ሃሳብ መሠረት እንዲቀጥል ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት ተማሪዎች ከወዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች አውቀው እንዲዘጋጁ ይገለፅላቸው ዘንድ እናሳስባለን።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
618 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 21:07:42 #Braking_news

በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የጸጥታ ችግር አጋጥሞ በነበረባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በ43ቱ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ187 ሺ በላይ ተማሪዎች ይገባሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው በእርማት ወቅት የነበሩ ስህተቶችን በወቅቱ አስተካክለናል፡ የሚሻሻል የነገር የለም ብለዋል።

https://t.me/ethio_aljezira
524 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 13:40:07 " ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/ethio_aljezira
456 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 13:39:10 " ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/ethio_aljezira
323 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 13:39:06 ''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መሰሪያቤቱ በዛሬው ዕለት ተገቢው ማብራሪያ እንደማሰጥ ገልጾልኛል ሲል አስታውቋል።

ቢሮው ''ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል። ከ12ኛ ክፍል ፈተና አኳያ የክልሉ ድርሻም ይሄው ነው።'' ሲል ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

''የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ በሚቀጥለው ቀን ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲስራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበናል። ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦችንም በወቅቱ አቅርበናል።'' ሲል ገልጿል።

አክሎም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ መረጃዎችን ሳልደብቅ ገልጻለሁ ብሏል።

''የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለሆነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም መሸፋፈንም አይቻልም።'' ማለቱን ከቢሮው ገጽ ተመልክተናል።

https://t.me/ethio_aljezira
279 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 14:25:04 #MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

https://t.me/ethio_aljezira
282 views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 21:03:27 #MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑን አስታወቀ።

በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው።

ከፍተኛ ውጤቱ በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑ ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ነው የተያዘው።

በአጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 287 ሺ223 ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/ethio_aljezira
299 views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 21:01:50 " በዚህ አመት 152 ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ይቀላቀላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺህ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287 ሺ 223 ናቸው ።

የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/ethio_aljezira
285 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:26:45 የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

https://t.me/ethio_aljezira
321 views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ