የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል ብሄራዊ ፈተናውን የምትፈተኑ ተማሪዎች እስከ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እስካሁን ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀረው ጊዜ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡ በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት አመራሮች በተለይም የት/ቤት ር/መምህራን ተፈታኝ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር አገልግሎቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ይገልጻል፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት @Ethiiostudents_bot Share share ለተጨማሪ መረጃ ╔═══════════╗ @Ethiio_Students @Ethiio_Students @Ethiio_Students ╚═══════════╝ 8.6K views08:50