Get Mystery Box with random crypto!

በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የስራ ኃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ 49 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በኦ | ሰበር !!

በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የስራ ኃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩ 49 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ ባልተገባቸው የእድገት ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ተብለው ከተጠረጠሩት ሰባ የመንግስት ሰራተኞች መካከል አርባ ዘጠኙ ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

በመምሪያው የጸረሙስና እና ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዋና ሳጅን ደርባባ ቶሎሳ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በተለያዩ የወረዳ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በሃላፊነት ቦታ ላይ ከሚገኙት ውስጥ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ተገልጿል፡፡

በዞኑ እየተደረገ ባለው ማጣራት እሳከሁን የጤና ፣የትምህርት፣ የመሬት ፣የመንጃ ፍቃድ እንዲሁም ሌሎች ሀሰተኛ ሰነዶች በተመሳሳይ መሰራታቸው በፍትህ አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑም ተነግሯል ፡፡

በመሆኑም የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስካሁን በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ በተደረገው ምርመራ ከተጠረጠሩት ሰባ ሰራተኞች መካከል አርባ ዘጠኙ ላይ ከሁለት አመት እስከ አራት ዓመት እስራት እንዲሁም ከአስር ሺህ ብር እስከ ሃምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መወሰኑን ዋና ሳጅን ደርባባ ቶሎሳ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiiostudents_bot

        Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
@Ethiio_Students  
╚═══════════╝