Get Mystery Box with random crypto!

'የሌብነት አምባሰደርነትን ትተን የሰላም አምባሳደር እንሁን' አቶ ዳይ ከንቲማ የማንዱራ ወረዳ ሰላ | Ethio Times®️

"የሌብነት አምባሰደርነትን ትተን የሰላም አምባሳደር እንሁን" አቶ ዳይ ከንቲማ የማንዱራ ወረዳ ሰላምና ግንባታ  ጽ/ቤት ኃላፊ

ግንቦት 26/2014 ዓ.ም(ኢትዮ ታይምስ)በአማራ ክልላዊ መንግስት እና በቤንሻንጉል ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬም በአዊ ብሔ/አስተዳደረ የጓንጓ ወረዳና የቻግኒ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በቤንሻንጉል ክልል የድባጢና የማንዱራ ወረዳዎች ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በሁለቱ ዞኖች አዋሳኝ በሆነው ካር በር ላይ እየተካሄደ ይገኛል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተፈጠረው ችግር  አማራ ሞቷል፣አገው ሞቷል፣ጉሙዝ ሞቷል፣ሽናሻ ሞቷል፣ ኦሮሞ ሞቷል ፤ የሆነውን ሁሉ ትተን ሰላም እንፍጠር ፤የሌብነት አምባሰደርነትን ትተን የሰላም አምባሳደር እንሁን ሲሉ አቶ ዳይ ከንቲማ በአፅንኦት አሳስበዋል።
መድረኩ የሁለቱ ዞኖች ብሔረሰብ ም/ቤቶች ከአሁን በፊት የተደረጉ መድረኮች ቀጣይ ሲሆን ሕዝቡ እንዲገናኝና የሰላሙም ባለቤት እንዲሆን ማድረግን ያለመ እንደሆኑ መድኩ ይጠቁማል።