Get Mystery Box with random crypto!

ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው። የደም ግፊት | ትንሳኤ ዘኢትኤል ጥበብ እና የባህል ህክምና መማማሪያያ

ደም ብዛት (Hypertension)
ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው። የደም ግፊት ደም በደም ቧንበዎች ውስጥ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀመው ሃይል ነው ግፊቱ ከፍ ባለ ቁጥር ልብ ደምን ለማሰራጨት ብዙ መስራት ይኖርበታል የላይኛው የደም ግፊት > 140mmHg የታችኛው የደም ግፊት > 90mmHg
ልብ
ልብ¥ የልብ ስራ ደምን ወደ ሰውነት መርጨት ነው ልብ አራት ክፍሎች አሉት የላይኛዎቹ ደም መላሽ (atrium) ሲባሉ የታችኞቹ ደግሞ (ventricle) ከርሰ ልብ በመባል ይታወቃሉ በያንዳንዱ ልብ ምት የቀኝ ከርሰ ልብ መጠኑ እኩል የሆነ ደም ወደ ሳምባ ይልካል፣ የግራው ከርሰ ልብ ደም ወደ ሰውነት ይረጫል። @ethel2011
#ልብ Cardiac output: ልብ በአንድ ግዜ ከቀኙ ወይም ከግራው ከርሰ ልብ የሚረጨው የደም መጠን ነው Afterload: ልብ ከግራ ከርሰልብ ወደ ሰውነት ለማሰራጨት የሚጠቀመው ሃይል ሲሆን Preload: ደግሞ ልብ ደምን ከመርጨቱ በፊት ያለው የልብ ጡንቻ የመለጠጥ አቅም ነው።
#ደም ብዛት ጤነኛ የደም ግፊት 120/80mmHg ነው የደም ግፊት ከ 140/90mmHg ካለፈ ደም ብዛት ይባላል። የደም ብዛት በአብዛኛው ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም የኩላሊት ደም ቧንቧ መጥበብ ደም ብዛት ያስከትላል። ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ፣ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ደም ብዛት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
#በእርግዝና ግዜ የሚያጋጥም ደም ብዛት ከ22 የእርግዝና ሳምንት በፊት የሚያጋጥም (pre existente hypertensie) ይህ አይነቱ የደም ብዛት የእርግዝናው ግዜ ሲጨምር አብሮ ከፍ ይላል። ይህ ደም ብዛት ከወለዱ ከ6 ሳምንት በሁዋላም ከቀጠለ ቀድሞም የነበረ ነበር ማለት ነው ።
#140/90mmhg) የእርግዝና ግዜ ደም ብዛት ለእናቱና ለሚወለደው ሕጻን የጤና ችግሮችን ያስከትላል ደም ብዛት በሽንት ፕሮቲን ከማስወገድ ጋር ካጋጠመ እርጉዟ ወደ ማህጸን ሐኪም ልትላክ ይገባል። @ethel2011
#ደም ብዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደም ብዛትን ሊያስከትሉ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ ውፍረት፣አልኮል፣ ሲጋራ፣ ማጤስ፣ ስኳር በሽታ፣ ያለመንቀሳቀስ፣ የካልሲየም፣ፖታሲየም፣ማግኔዚየም እጥረት ብስጭት፣ጭንቀት፣ እርጅና ወዘተ...
#ደም ብዛት እድሜ እየጨመረ ሲመጣ የደም ብዛት የማጋጠም እድልም ከፍ ይላል።
ምት (stroke (CVA))በደም ብዛት ምክንያት ከሚያጋጥሙ በሽታዎች አንዱ ነው።
ከ 40-59ዓመት ወንዶች የላይኛው የደም ግፊታቸው ከ 160-180mmHg ከሆነ ጤነኛ የደም ግፊት ካላቸው ወንዶች በአራት እጥፍ ሞት ያጋጥማቸዋል ደም ብዛት ልብ ድካምንና የልብ ጡንቻ መሞትን (heart attack) ያስከትላል።
#ደም ብዛት ማጨስና የስብ (ኮሌስቴሮል) መብዛት ከደም ብዛት ጋር ካጋጠሙ የሞትና የልብ በሽታ እድል በጣም ከፍ ይላል አልኮል የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል።
#ይህ ሳይነስ የደረሰበት ዘመናዊ ሊቃውንቶቻችን የከተቡት የደም ብዛት መንስኤ እና ምልክቶች ናቸው።
እኔ ግን እላለሁ ይህ እንዳለ ሁኖ! የኛዎቹ ቀደምቶቹ የጥበብ ሊቃውንቶቻችም የደም ግፊት(ብዛት) ከትውልድ የመተላለፍ ዕድሉ ሰፊ የሆነ በሽታ ነው። እንዲሁም በክፉ የሰው ልጅ ጠላቶች የዛር መናፍስት እንደሚከሰትም ይጠቁማሉ። @ethel2011
የደም ብዛት መፍትሔ
#የእንጭብር ሥር እና ቅጠል
እንጭብር አረም መሳይ ሁኔታው ወደ ሐረግ የሚያደላ ከ 40-60 ሳሜ የሚረዝምና ቅጠሉ አረንጓዴ፣ አበባው ነጭ ነው።
ግንዱ እና ቅጠሉ ሸካራ እና የሚኮሰኩስ፣ሥሩ ወይንጠጅ፣ቀላ ያለ ሥር አለው።
ለአስም፣ለንቃተ ሕሊና፣ለደም ግፊት መዳኛ ይሆናል። @ethel2011
ዛሬ ለደም ብዛት መፍትሔ እና አጠቃቀም የምጠቁማችሁ ይሆናል።
የእንጭብር ሥር በብዛት አዘጋጅተው አድርቀው በደንብ አድርገው ፈጭተው በወንፊት በመንፋት ያዘጋጁ።
ከተነፋው ዕጽ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት በግማሽ ሌትር ወተት አብሮ በማፍላት ትንሽ ቀዝቀዝ ሲል ጧት እና ማታ ከምግብ በፊት ይጠቀሙ።ከተገኘ የአርማጉሳ ወይም የጡት አስጥል ቅጠል በትንሿ የስኳር ማንኪያ አንድ ይጨምሩበት።
ይህ ድርጊ አንድ አንድ ቀን እየዘለሉ ለ ሁለት ወራት ያክል ይጠቀሙ ዕፁ ከጎንዮሽ ጉዳት ውጭ የሆነ ዕጽ ነው። በተለያዩ ክፍለ ሃገራት ለቅመምነት ፣ለምግብ ቀለም፣ለምግብ ዘይት፣ለውስጥ ደዌ ፣በዱቄት መልኩ ተዘጋጅቶ በብዛት በውድ ዋጋ የሚሸጥ መልካም ዕፅ ነው።
#በደም ግፊት ሕይወታቸው ለሚያጡ ውድ ኢትዮጵያውያን ይሁንልኝ።
ሼር በማድረግ ለመላው የዓለም ህዝብ እናድርስ መልካም መፍትሔ ነውና።