Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ አፈፃፀም 76 ከመቶ ደረሰ   | Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp

የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ አፈፃፀም 76 ከመቶ ደረሰ
              
አጠቀላይ የፕሮጀክት ስራውን በአንድ መቶ አስር ሺ ካሬ  ሜትር  መሬት ላይ  ለማሳረፍ በሶስት የግንባታ ምዕራፍ (3 phase) እቅድ ተይዞ እተሰራ ከሚገኘው ከዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት ግንባታ መካከል የመዕራፍ አንድ ( 1 phase) ግንባታ ስራ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ተገልፅዋል፡፡

በአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ሰጪ በላሙያ የሆኑት ታደለ ዳንደና (ኢ/ር ) እንደገለፁት በከተማው አስተዳደር ልዩ ትኩረት የተሰጠው እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቶሎ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ተገቢ የሆነ የቴክኒክ ድጋፍና ክትትል  ሥራ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የፕሮጀክት ግንባታው ክትትል ስራ አስኪያጅ ጌትነት በሻህ (ኢ/ር) በበኩላቸው  አዲስ አበባን የምስራቅ አፍሪካ የግብይት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ የሚገኘው ይህ ትልቅ የግንባታ ፕሮጀክት ከክብርት ከንቲባዋ ጀምሮ በከተማው አስተዳደር ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት እና ሌሎች አካላት ብርቱ የድጋፍና ክትትል ስራ አማካኝነት  የፕሮጀክቱ ግንባታ አፈፃፀም 76 ከመቶ ደርስዋል ብለዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ አክለውም በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች ሳቢያ የፕሮጀክት ግንባታው ሳይጠናቀቅ ቢዘገይም ፤ የከተማው አስተዳር ለፕሮጀክቱ በሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል አሁን ላይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው ያስቻለ ስለሆነ፤በቀጣይም እስከ ፕሮጀክቱ ፍፃሜ በየደረጃው ያለ የከተማው አስተዳደር አካል ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል  ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሽርክና ወይም በአጋርነት ከሚያስገነባቸው የመዲናዋ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል፣ የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ዋንኛው ሲሆን፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ  በከተማዋ ሁሉን አቀፍ ገፅታ ላይ የጎላ  አስተዋጽኦ ከማድረግ ባሻገር  ለሀገራችን ዜጎች በተለያየ የሙያ መስክ በቋሚና ጊዚያዊነት  ሰፊ የስራ እድል ይፈጠራል  ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via አአሜጋፕ

@etconp