Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2,877,560 ኩንታል ምርትና አገልግሎት | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2,877,560 ኩንታል ምርትና አገልግሎት ለገበያ አቀረበ

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ብር 9,046,004,247 ዋጋ ያለው 2,877,560 ኩንታል ምርትና አገልግሎት በማሰራጨት ዕቅዱን በመጠን 90 በመቶ በዋጋ ደግሞ 79 በመቶ አከናውኗል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የሽያጭ መጠን ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ ከተገኘው ጠቅላላ ሽያጭ ገቢ 99.14 በመቶ ከሀገር ውስጥ ሽያጭ ገቢ የተገኘ ሲሆን ቀሪው 0.86 በመቶ ከኤክስፖርት የተገኘ ገቢ ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለሃገር ውስጥ ገበያ ብር 8,713,617,305 ዋጋ ያለው 2,832,037 ኩንታል ምርት እና አገልግሎት በማሰራጨት የዕቅዱን በመጠን 92 በመቶ በዋጋ ደግሞ 81 በመቶ አከናውኗል፡፡ የሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች በገቢ ድርሻ ሲታይ፡- እህልና ቡና 69.1%፣ የምግብ ዘይት 14.7%፣ ፍጆታ ዕቃዎች 6.7%፣ የኮንስትራክሽን ግብአቶች 5.27%፣ አትክልትና ፍራፍሬ 4.1 እና የግዥ አገልግሎት ሽያጭ 0.1 በመቶ ድርሻ ነበራቸው፡፡

የውጭ ሀገር ሽያጭን በተመለከተ በዘጠኝ ወራት 6,577 ኩንታል የተለያዩ የብርዕ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና እና ፍራፍሬ ሽያጭ በማድረግ 1,484,488 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከአምራቾች የገዛውን ምርት በቀጥታ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የአቅርቦት ዕጥረት ለመከላከል ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በሀገር ውስጥ ግብይት ለህብረተሰቡ ያቀረባቸው ምርቶች ከነፃ ገበያ ዋጋው ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ነበረው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ለህብረተሰቡ የሸጠውን ብር 7.57 በሊዮን ዋጋ ያለው ምርት በወቅቱ በነበረው የገበያ ዋጋ ቢሽጥ ሊያወጣ ይችል የነበረው ዋጋ ብር 12.24 ቢሊዮን እንደሆነ ይገመታል፡፡ በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኮርፖሬሽኑ የሸጠው አጠቃላይ ምርት ዋጋ ከገበያው ዋጋ በብር 4.67 ቢሊዮን የቀነሰ መሆኑ ተመልከቷል፡፡