Get Mystery Box with random crypto!

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የሚከታተል ግብረ ኃይል | ETHIO STUDENTS NEWS™

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የሚከታተል ግብረ ኃይል አቋቋመ።
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ለመክፈት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ኮሌጁን እውን ለማድረግ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ለመገምገም ከነሀሴ 4-5/2014 ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙህራን፣ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምሁራን፣ ከደባርቅ ሆስፒታል ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በ2015 ዓም አዲስ በሚከፈቱ የነርሲንግና ስነተዋልዶ(Midwifery) ትምህርት መስኮች ከስርዓተ ትምህርትና ሰው ሀይል፣ ከግብአትና የክህሎት ማጎልበቻ ላብራቶሪ ከማቋቋም አንጻር የዩኒቨርሲቲውና የባለድርሻ አካላት ዝርዝር ሀላፊነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል።
ከውይይቱ ጎን ለጎን የነርሲንግና ስነተዋልዶ ትምህርት መስኮች የተማሪዎች የክህሎት ማጎልበቻ ላብራቶሪ ክፍሎች የተለዩ ሲሆን በቀጣይ ከዩኒቨርስቲው ጋር በአጋርነት ሊሰሩ የሚችሉ የህክምናና የትምህርት ተቋማትን የመለየት ስራ ተሰርቷል።
በመጨረሻም ከቅድመ ዝግጅት እስከ ተማሪዎች ቅበላ ያለውን ስራ በበላይነት የሚከታተል ግበረ ሀይል ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ከደባርቅ ሆስፒታልና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣ ምሁራንን ያሳተፈ ኮሚቴ በማቋቋም ዝርዝር እቅድ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

መረጃው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ነው

@ET_STUDENT_NEWS