Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO STUDENTS NEWS™

የቴሌግራም ቻናል አርማ et_student_news — ETHIO STUDENTS NEWS™ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ et_student_news — ETHIO STUDENTS NEWS™
የሰርጥ አድራሻ: @et_student_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.42K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-12 11:41:45
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የሚከታተል ግብረ ኃይል አቋቋመ።
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅን ለመክፈት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ኮሌጁን እውን ለማድረግ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ለመገምገም ከነሀሴ 4-5/2014 ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙህራን፣ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምሁራን፣ ከደባርቅ ሆስፒታል ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በ2015 ዓም አዲስ በሚከፈቱ የነርሲንግና ስነተዋልዶ(Midwifery) ትምህርት መስኮች ከስርዓተ ትምህርትና ሰው ሀይል፣ ከግብአትና የክህሎት ማጎልበቻ ላብራቶሪ ከማቋቋም አንጻር የዩኒቨርሲቲውና የባለድርሻ አካላት ዝርዝር ሀላፊነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል።
ከውይይቱ ጎን ለጎን የነርሲንግና ስነተዋልዶ ትምህርት መስኮች የተማሪዎች የክህሎት ማጎልበቻ ላብራቶሪ ክፍሎች የተለዩ ሲሆን በቀጣይ ከዩኒቨርስቲው ጋር በአጋርነት ሊሰሩ የሚችሉ የህክምናና የትምህርት ተቋማትን የመለየት ስራ ተሰርቷል።
በመጨረሻም ከቅድመ ዝግጅት እስከ ተማሪዎች ቅበላ ያለውን ስራ በበላይነት የሚከታተል ግበረ ሀይል ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ከደባርቅ ሆስፒታልና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣ ምሁራንን ያሳተፈ ኮሚቴ በማቋቋም ዝርዝር እቅድ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

መረጃው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ነው

@ET_STUDENT_NEWS
454 viewsedited  08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 14:44:45 ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት መፅሃፍም ሆነ ደብተር መሸጥ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተሰጠ

አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ሲል የ #አዲስአበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ እንደሚገኝም ኃላፊዋ አክለዋል። በመመሪያ አተገባበሩ ላይ ከመጡት ጥቆማዎች ውስጥ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መቀበል ለአብነት እሽግ ወረቀት እና የመፀዳጃ ቤት የንፅህና እቃዎችን የሚጠይቁ እንዳሉበት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ባልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ ያሉ የትምህር ተቋማት እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል ወርደን እናስተካከልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻሉም፤ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ብለዋል።ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በሚገኝ ተቋም ላይ ርምጃ ይወሰድበታል፤ የሰበሰበውን ገንዘብም ሆነ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ እንዲመልስ ይደረጋል ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS
676 views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 17:26:27
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ የአካባቢው ተማሪዎች የክረምት ስልጠና እየሰጠ ነው።

በስልጠናው ከጋሞ እና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከደራሼ፣ ባስኬቶ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ተማሪዎች እየተሳተፉ ናቸው።

ስልጠናው ለ45 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ሒሣብ እና ኤሌክትሮኒክስና ICT ትምህርት አይነቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

@ET_STUDENT_NEWS
883 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 13:18:37
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ የአካባቢው ተማሪዎች የክረምት ስልጠና እየሰጠ ነው።

በስልጠናው ከጋሞ እና ጎፋ ዞኖች እንዲሁም ከደራሼ፣ ባስኬቶ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ተማሪዎች እየተሳተፉ ናቸው።

ስልጠናው ለ45 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ሒሣብ እና ኤሌክትሮኒክስና ICT ትምህርት አይነቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

@ET_STUDENT_NEWS
964 views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 09:47:43
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም እየሠራ ይገኛል።

FM 103.5 የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያው፤ ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የመማር ማስተማር እንዲሁም የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል ታምኖበታል።

በኢትዮጵያ 12 ዩኒቨርሲቲዎች የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ያላቸው ሲሆን አራት ዩኒቨርሲቲዎች የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም እየሠሩ ይገኛሉ።

@ET_STUDENT_NEWS
970 viewsedited  06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 15:48:30
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ሙሉ በሙሉ ውድመት የደረሰበት የቆቦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን የተግባር ሥልጠና የሚያስፈልጋቸውን ትምህርቶች መስጠት እንደማይችል አስታወቀ።

ኮሌጁ የተግባር ሥልጠና የሚያስፈልጋቸውን ትምህርቶች ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የማይችለው፣ በጦርነቱ የወደመውን የተግባር ሥልጠና መስጫ ማሽነሪዎች መተካት ስላልቻለ መሆኑን የኮሌጁ ዲን ደሳለኝ አደም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ኮሌጁ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 810 ማሽነሪዎች ሙሉ በሙሉ እንደወደመበት የገለጹ የኮሌጁ ዲን፣ ከአይሲቲ ትምህርት ውጭ የተግባር ት/ት ባለመስጠቱ በዓመት መቀበል ከሚችለው 1 ሺሕ 500 ተማሪ አሁን ላይ መቀበል የሚችለው 500 ተማሪ ነው ብለዋል።

ኮሌጁን ለማቋቋም ከክልል እስከ ፌደራል የተሰየሙ የመንግሥት ተቋሞች፣ በታቀደው ልክ ድጋፍ እያደረጉ አለመሆኑን ደሳለኝ ጠቁመዋል። መንግሥት የወደሙ ተቋሞችን መልሶ ለማቋቋም የትስስር ሥራ ቢፈጥርም በተግባር የሚታየው ድጋፍ አነስተኛ ነው ተብሏል።

የራያ ሰላምና ልማት ማኀበር ኮሌጁን ለማቋቋም ለኹለተኛ ጊዜ የኮምፒውተር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ማኀበሩ ያደረገው ድጋፍ ኮሌጁ መልሶ ለማቋቋም መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ኮሌጁ ከዚህ ቀደም የተቀበላቸውን ተማሪዎች የተግባር ሥልጠና ሳይሰጥ ለተማሪዎች ሞራል ሲል ለማስመረቅ መገደዱን አስታውቋል። ኮሌጁ አሁን ላይ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ሆኖ እያገለገለገለ ይገኛል።

ኮሌጁን መልሶ ለማቋቋም በትስስር የተመደቡ ተቋማትና መንግሥት እንዲሁም ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ማኅበሩና ኮሌጁ ጠይቀዋል።

አዲስ ማለዳ
@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS
1.8K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 22:10:02
#የትምህርት_እድል

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል።

የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 78 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ09/12/14 - 13/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• የመመዝገቢያ ብር 400
• አንድ ክላሰር ይዛችሁ ተገኙ

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ተብሏል።

@ET_STUDENT_NEWS
1.7K viewsedited  19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:42:00
በመጪው መስከረም ራስ ገዝ የሚሆነውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ሳይጨምር በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታትም 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ መንግሥት አቅጣጫ ማስቀመጡን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ፒኤችዲ) እንደገለጹት በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ትግበራው ለትምህርት ጥራት፣ በተቋማቱ መካከል የትብብር እና የፉክክር መንፈስ በማምጣት ልሕቀትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ጠቁመው በዚህ ምክንያትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲን ዕውን ለማድረግ ይረዳል ብለዋል፡፡

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ሲሆኑ ተወዳድረው ከውጭም ሀብት ያገኛሉ፤ ከአገር ውስጥ ከንግዱም ማኅበረሰብ በምርምርና በማማከር ገቢ ያስገባሉ፤ ብቁ ተማሪ ስለሚያወጡ ከመንግሥትም ተጨማሪ በጀት ያገኛሉ።

ውድድሩ ልህቀት ያመጣል፤ የትምህርት ልህቀት በአገር ውስጥ አይገደብም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ተቋም መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

ለመምህራኖቹ የተሻለ የደመወዝ ክፍያ እና ጥቅማ ጥቅም አሟልተው እንዲቀጥሩ የሚያስላቸው እንደሚሆን ጠቁመው ለሚቀጥሯቸው መምህራን እንደ አቅማቸው የሚከፍሉበት ዕድል ይሰጣቸዋል ብለዋል።

@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS
1.4K viewsedited  17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 13:03:41 ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ይጀምራል

ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በሚጀምረው አዲሱ ስርአተ ትምህርት ( ካሪኩለም) መሰረት ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ፈተና መውሰድ የሚጀምሩ ይሆናል።

ለሁሉም ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ከተላከ ፋይል እንደተረዳነው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካላንደር የተገለጸ ሲሆን ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 16 /2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ሁሉም ተማሪዎች የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ሲወስዱ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በልዩ ሁኔታ የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መውሰድ ይጀምራሉ።

በ2009 ዓ.ም የመጨረሻው የ10ኛ ልፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከተሰጠ እና የ10ኛ ክፍል መልቀቂይ ብሔራዊ ፈተና ( ማትሪክ) መሰጠት ካቆመና ተማሪዎች በክፍል ውጤታቸው ብቻ ማለፍ ከጀመሩ ወዲህ ጥቂት ጊዜያት በኋላ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት እንደሚጀምር ሲገለጽ ቆይቶ ነበር።

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS
1.5K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 13:01:58
#BREAKING_NEWS
የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

Via:TIKVH ETHIOPIA

ስለ ዩኒቨርስቲ መረጃ ከፈለጋችሁ ሼር አድርጉ ።
ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@ET_STUDENT_NEWS
@ET_STUDENT_NEWS
1.4K viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ